በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ሀኪም ቁጥር አራት ብቻ ናቸው

Date:

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በሰፊው እንደሌለ እና የህፃናት የሳይካትሪስት ባለሞያዎች ቁጥር በስፔሻሊስት ደረጃ ያሉ ከባድ ህመሞችን የሚያክሙ ባለሞያዎች ቁጥር 4 ብቸ መሆናቸው ተገልፀዋል፡፡

የህፃናት የአዕምሮ ህክምና በሁሉም ሳይካትሪስቶች ይታከማል ነገር ግን በጣም ከፍተኛ ለሆነ ህመም ግን የሚያክሙት ባለሞያዎች አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ በጥቁር አንበሳ እና በጳውሎስ ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኚ ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት በጤና ሚኒስቴር ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች እና የአዕምሮ ጤና ፕሮግራም ባለሞያ አቶ ጀማል ተሾመ ናቸው፡፡

በኢትዮጶያ ውስጥ ከ1ሺ 900 በላይ የአዕምሮ ጤና ባለሞያዎች አሉ፡፡ነገር ግን ይሄ ቁጥር ሁሉንም አገልግሎት የሚሰጡ ባለሞያዎችን ጨምሮ ነው ብለዋል፡፡በሀገራችን የአዕምሮ ጤና ባለሞያዎች ቁጥር ከታካሚዎች አንፃር አነስተኛ እና ገና የሚባል ደረጃ ላይ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በሀገራችን የመጀመሪያ ዲግሪ ሳይካትሪስት  ቁጥር ከ2ሺ በላይ ያለ እና በሙያው የሰራተኛው ሀይል ገበያ ላይ ቢኖርም እየተጠቀምንበት ግን አይደልም ብለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደ ምክንያት ያነሱት ከሀገር አቅም አንፃር ወይንም ከግንዛቤ እጥረት አንፃር ሊሆን እንደሚችልም ገልጸዋል፡፡ነገር ግን እነዚህ ባለሞያዎች ወደ ዘርፉ ቢቀላቀሉ ትልቅ የአዕምሮ ጤናን ከፍ ከማድረግ  እና ሽፋንን ከመጨመር አንፃር ትልቅ አስተዋፅዎ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

በአዕምሮ ጤና ህክምና ከ15 እስከ 64 እድሜ ያሉ ሰዎች ተጎድተው ይታያሉ፡፡አብዛኞቹ ግልፅ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ከ15 ዓመት ጀምሮ የሚጀምሩ መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ ለኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ደብዳቤ ላከች

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ለኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር...

ዓመታዊ ግብርን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማሳወቅና መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ተዘረጋች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከእንግዲህ የደረጃ «ሀ» ግብር...

62ኛው የባህል ማዕከል ምሽት አንጋፋዋን ጋዜጠኛ የመዓዛ ብሩን ዘክሯል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፥ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ...

የከተማ መሬት የሚከፋፈልበት ስርዓት መሻሻል እንዳለበት ተጠቆመ

  የከተማ መሬት አስተዳደር ከሙስና እና ጥቅማ ጥቅም ጋር እየተያያዘ...