በእንግሊዝኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት የተማሩ ከ100 በላይ ታዳጊዎች ተመረቁ

Date:

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት በቦሌ ኆኀተ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ላለፉት አምስት ሳምንታት በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሠረታዊ የቤተክርስቲያን ትምህርት ሲከታተሉ የቆዩ ከ100 በላይ ታዳጊዎችን ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ፣ የመገናኛ ብዙኃኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ቀሲስ አካልወልድ ተሰማ እና የተመራቂዎቹ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

ተማሪዎቹ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ታሪክ እና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የተማሩ ሲሆን፣ መርሐ ግብሩ እምነቱን ለወጣቶች ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ባለው መልኩ ለማስተላለፍ በማሰብ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት፣ ታዳጊዎች የእምነታቸውን ትምህርት በእንግሊዝኛ መማራቸው ወደፊት በውጭ ሀገራት ቢኖሩም እምነታቸውን በቀላሉ እንዲረዱና እንዲያስተምሩ እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅትም የወንጌል ትምህርቶችን በተለያዩ ቋንቋዎች ተደራሽ የማድረግ ሥራውን በቀጣይነት እንደሚያጠናክር አስታውቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በዓለም የምግብ ምርምር ድርጅት ሹመት ተሰጣቸው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአግራ (AGRA) የቦርድ ሰብሳቢ...

አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በካናዳ ሀገር ሊሸለሙ ነው

የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በንግዱ...

በምክክሩ ወቅት በሀሳብ ልዩነት “አድማ የመቱ” ነበሩ

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ22ኛው ቀን ውሎው በስልታዊ ቡድን ደረጃ...

በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለዉ ግጭት እንዳሳሰበው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን ገለፀ

የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን  በኢትዮጵያ ፌደራላዊ  መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ...