አይኤምኤፍ ግን የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በባህረ ሰላጤው ውጥረት ምክንያት ለችግር ተጋልጠው እንደሚቀጥሉ አስጠነቀቀ
በጅቡቲ ወደብ ሦስት ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች መድረሳቸው የተሰማ ሲሆን፣ ይህም በኢትዮጵያ ለተከሰተው የነዳጅ እጥረት መጠነኛ እፎይታ ሊሰጥ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል።
ከመጋቢት 19 እስከ 23 ባሉት ጊዜያት ዉስጥ በጅቡቲ የደረሱት እነዚህ መርከቦች በአጠቃላይ 143,000 ሜትሪክ ቶን የሚመዝን ናፍጣና የጄት ነዳጅ የጫኑ መሆናቸውን ካፒታል ለመረዳት ችሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በባህረ ሰላጤው አካባቢ ባለው ውጥረት ምክንያት አሁንም ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ተጋልጠው እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቋል።
እንደ አይኤምኤፍ ትንታኔ ከሆነ፣ በባህረ ሰላጤው የሚታየው አለመረጋጋት የንግድ ልውውጥን በማስተጓጎልና የጭነት ዋጋን በመጨመር በቀጣናው ሀገራት ላይ የዋጋ ንረትን ሊያስከትል ይችላል።
