ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ሰው-ተኮር የሆኑ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ በአፍሪካ ህብረት ባዘጋጀው ክብረ በዓል ላይ አስታውቋል::
የዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ዘላለም አማረ እንደገለፁት ት/ ቤቱ ይህን 20ኛ አመት በአል ሲያክብር ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ለሌሎች ት/ቤት ለ1600 ለሚቆጠሩ ተማሪዎች የንጹህ ውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ በማስጀመር በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
ይህም ተማሪዎቹ በሁለት እና በሦስት ሮቶ የውኃ ማቆሪያ ብቻ ሳይሆን በነጻነት ለንጹህ የመጠጥ ውኃ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ብለዋል::
አቶ ዘላለም አክለውም የት/ቤቱ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ አስተዳደርና ሰራተኞች እንዲሁም አዲስ ህይወት የድራግ ሪ ሀቢሊቴሽን ሴንተር ከተባለ ድር ጅት ጋር በመሆን ለሙዳይ በጎ አድራጎት ድርጅት የገንዘብና ሌሎች የግልጋሎት ዘርፎችን ማድረጉን ገልጸዋል::
በመርሀግብሩ ከት/ቤቱ ራዕይና ተልኮ ተመሣሣይነት ባለው ሁኔታ የዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ በሆኑት አቶ ዘላለም አማረ የተፃፈ “እያንዳንዱ ልጅ የዓለም ብርሃን የመሆን እምቅ ኃይል አለው!” Every child is potentially the light of the world” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ መጽሐፍ ቀርቧል::
በፕሮግራሙ የሚዲያ ባለሙያዎችን ጨምሮ የመንግሥት አካላት ተወካዮች፣ አጋርና ተባባሪ አካላት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን፣ የት/ቤት አመራሮች፣ ወላጆች፣ መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተዋል::
ከተመሠረተ 20ኛ ዓመቱን የያዘው ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል ከ400 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል እንደሰጠ የተገለፀ ሲሆን ከ1 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል ::በቀጣይም ይህ ነፃ የትምህርት እድል ለእያንዳንዱ ተማሪ እንደሚዳረስ ተጠቁሟል:: ድሬቲዩብ
