Home Featured በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በኢትዮጵያ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን ሪፖርት አመለከተ

በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በኢትዮጵያ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን ሪፖርት አመለከተ

በጎርጎሮሳውያኑ 2024 በኢትዮጵያ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን ሪፖርት አመለከተ

የጋዜጠኞች ደህንነት ግምገማ በማካሄድ የሚታወቀው አለም አቀፉ የሚዲያ ድጋፍ ተቋም ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ በጎርጎሮሳውያኑ 2024 ብቻ 43 ጋዜጠኞች ለእገታ እና እስር መዳረጋቸውን አስታወቀ። ሪፖርቱ ጋዜጠኞች ከመንግስት እና መንግስትዊ ካልሆኑ አካላት ማስፈራሪያ፣ እስር እና እንግልትን ጨምሮ ለበርካታ ጫናዎች ተጋላጭ መሆናቸውን አመላክቷል።

ከ60 ጋዜጠኞች ጋር በተደረገ ቃለ መጠይቅ እና በሰነድ በተመዘገቡ ጉዳዮች ላይ የተመሠረተው ሪፖርቱ፣ በግጭት በተጎዱ አካባቢዎች ያሉ ጋዜጠኞች በተለይም በ አማራ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ከፍተኛ አደጋ እንደሚገጥሟቸው አረጋግጧል።

በሪፖርቱ መሠረትም “የታጠቁ ቡድኖች ጋዜጠኞችን የቤዛ ክፍያ ለመቀበል ወይም ስለግጭቶች የሚወጡትን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባዎችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ቁሳቁሶቻቸውን ለመወሰድ በማሰብ በዘፈቀደ አስረዋል።  በሌላ በኩል የመንግስት ባለሥልጣናት ደግሞ “ብሔራዊ ደህንነት እና ብሔራዊ ጥቅም” በሚል ሰበስ ጋዜጠኞች እንዲታሰሩ ማድረጋቸውን ሪፖርቱ አመላክቷል።

@ አዲስ ስታንዳርድ