ባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴዎች ዘላቂ ሰላም

Date:

በጋምቤላ ክልል ዘላቂ ሰላም ለማስፈን በማኅበረሰብ መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን በባህላዊ የግጭት አፈታት ዜዴ መፍታት እንደሚገባ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች አመለከቱ። ከዚህ በተጨማሪ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር በክልሉ አዋሳኝ ቦታዎች የሚስተዋል በመሆኑ ታጣቂዎች መሣሪያ በቀላሉ እንደሚያገኙ አመልክተዋል።

 
 በክልሉ ለዘመናት አብረው በኖሩ ማኅበረሰቦች መካከል አለመግባባት ለመፍጠር በቡድንና በግለሰብ ደረጃ  የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ኃይሎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች መፈጸማቸውን በመግለጽ በክልሉ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን  እነዚህን ችግሮች ከምንጩ መፈታት እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ከተለመደው ሕዝባዊ ጉባኤ በተጨማሪም ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓት ችግሩን ከመፍታት አንጻር የጎላ ሚና እንዳላቸው በክልሉ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ አዶል አጉዋ ጠቁመዋል።
‹‹በማኅበረሰቡ መካከል የሚከሰቱ አለመግባባቶችን ከምንጩ መፍታት››


በጋምቤላ ክልል ከዚህ ቀደም በነበሩ ማንነትን መሠረት ያደረጉ ናቸው የተባሉ ጥቃቶች በርካታ ሰብአዊና ሌሎች ጉዳቶችን ማድረሱ ተዘግበዋል። ከጥር ወር 2018 ዓ.ም አንስቶ ደግሞ የክልሉ የጸጥታ ችግር ለመቅረፍ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ወይም ኮማንድ ፖስት ሁሉንም የክልሉ መደበኛ እና አድማ ብተና ፖሊሶች ወደ ዳግም ስልጠና እንዲገቡ አድርገዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል የሀገር ሽማግሌ የሆኑት አቶ ኦዶል አጉዋ የክልሉን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ከፖሊሶች ስልጠና በተጨማሪ በማኅበረሰቡ መካከል የሚከሰቱ ግጭቶችን ከምንጩ መፍታት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።


በተለያዩ ወቅቶች ከፖለቲካ ጥያቄ እና የመሬት ይገባኛል ጥያቄዎችጋር ተያይዞ የተለያዩ አለመግባባቶች እንደሚፈጠሩ የገለጹት አቶ ኦዶል የተሳሳቱ የማኅበራዊ መገናኛ ዜዴ መረጃዎች ስርጭትም በወጣቱ ዘንድ በጉልህ እየታየ ያለና አልፎ አልፎ ለሚከሰቱ ግጭቶች እንደመንስኤ የሚጠቀስ ነው ብለዋል።
 
በክልሉ ሌለው የሀገር ሽማግሌ የሆኑ እና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ነዋሪ ከዚህ ቀደም ከፖለቲካ ሥልጣንና ከመሬት ይገበኛል ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች አለማግግባት መፍጠሩንም ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በአካባቢው አብሮ የሚኖሩ የኑዌርና አኙዋ ማኅበረሰቦች መካከል ቅራኔ ለመፍጠር በማኅበራዊ መገናኛ ዜዴ ይሰራጫሉ ያሏቸው የጥላቻ ንግግሮችም ለተከሰቱ ግጭቶች ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡

እነዚህ ይሰራጫሉ ያሏቸው የጥላቻ ንግግሮችም አንዱ የማኅበረሰብ ክፍል በመነጠል ለጥቃት የሚዳርግ መሆኑን በመግልጽ ይህንን ከሁለቱ  የአኙዋ እና ኑዌር ማኅበረሰብ ጋር በባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓትም ሆነ ባህላዊ ዘዴ በዘላቂነት መፍታት እንደሚቻል ጠቁመው፣ በክልሉ ዘላቂ ሰላም ያጣል ያሉትን ሀሳብ አብራርተዋል።


የጋምቤላ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሽኔ አስቲን ባለፈው ሳምንት በሰጡን ማብራሪያ በክልሉ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ቀዳሚው የክልሉ ዕቅድ መሆኑን አብራርተዋል። በክልሉ የሚኖሩ የተለያዩ ማኅብረሰብ ክፍሎችን መካከል ያለውን ማኅበራዊ መስተጋግብር ለማጉልበት እንደሚሠራም ጠቁመዋል።


በክልሉ ከዚህ ቀደም በነበሩት አለመግባባቶች ውስጥ ተሳትፈዋል የተባሉ ከ40 በላይ የፖሊስ አባላት በሕግ ተጠያቂ መሆናቸውን በመጋቢት ወር የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጹ ተዘግበዋል። እነዚህ በሕግ ተጠየቁ የተባሉ የፖሊስ አባላት በስነ ምግባር ችግር፣ ብሔርን ወግኖ ጉዳት ማድረስ፣ በሙስና እንዲሁም የጦር መሣሪያ ይዞ መሸሽና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ተሳታፊ የሆኑ ናቸው ተብሏል።

DW

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዜጋዬ ተገድሏል ያለችው ጋና ከደቡብ አፍሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ውስጥ ገባች

አንድ ጋናዊ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ካለው ፀረ ስደተኞች ተቃውሞ...

«የማይናገረው ልዑል» መጽሐፍ በታላቅ ድምቀት ሊመረቅ ነው

ደራሲ መሠረት ክንፈ ኃይሌ ከኦቲዝም ጋር ከሚኖረው ልጇ ልዑል...

በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚደረግ ንግድ በገንዘብ መጠን ተገደበ

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኢትዮጵያ እና በኬንያ ድንበር የሚከናወነውን...

(IMF) ከ460 ሚሊዮን ዶላር በላይ ብድር አፀደቀ

አዳዲስ ብድር በመውሰድ ረገድ ጥንቃቄ እንድታደርግ ኢትዮጵያን ያስጠነቀቀው IMF...