ባንኩ ከ264 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለደንበኞች አቅርቧል

Date:

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ስምንት ወራት ከ264 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለደንበኞች ማቅረቡን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።

717 ሺህ ደንበኞች በዲጂታል አማራጭ የብድር ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውንም አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተቋሙን የስምንት ወራት አፈጻጸም ለህዝብ ተወካዮች ተወካዮች ምክር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ባንኩ ብድርን ከማስፋፋት እና የዜጎችን የፋይናንስ ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር አዳዲስ የብድር አይነቶችን እያስተዋወቀ ይገኛል፡፡

በዚህም ባንኩ ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ 264 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር ብድር ለደንበኞቹ ማቅረቡን ገልጸው ከዚህ ውስጥ 88 ነጥብ 2 በመቶው የተሰጠው ለግሉ ዘርፍ እንደሆነ አመልክተዋል።

ጠቅላላ የተሰጠ የብድር መጠን ብር 1 ነጥብ 39 ትሪሊዮን በር መድረሱንም ጠቁመዋል።የብድር ተደራሽነትን ከማስፋት አንፃር ባንኩ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር በዲጂታል አማራጭ ብድሮችን እያቀረበ መሆኑን ነው ያስረዱት።

ፕሬዝዳንቱ በዲጂታል አማራጭ ባለፉት ስምንት ወራት አጠቃላይ ብር 3 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብድር ማቅረብ መቻሉንና በፈረንጆች እስከ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2025 ድረስ 717 ሺህ ደንበኞች ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።ባንኩ የዜጎችን የስራ ተነሳሽነት ከመደገፍ አንጻር ጥሩ የመስራት አቅም ላላቸው ስራ ፈጣሪዎች የብድር አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉንም ጠቁመዋል።

በዲጂታል አማራጭ የብድር አገልግሎትን ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ የዝግጅት ስራዎች ተጠናቀው በሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ፕሬዚዳንቱ መግለጻቸውን ከባንኩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...