ብልጽግና እና የዐፄ ፋሲል ቤተ መንግሥት ፖለቲካ‼

Date:

ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ

    የሀገርና የወገን የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የአንድ ሀገር የቀደመ ትውልድ ሁለንተናዊ ገጽታና ማንነት ማሳያ መነጽሮች  ናቸው። በተለይም በዓለም አቀፍ የቅርስ ጥበቃ እውቅና የተሰጣቸው ቅርሶች ሀገርን ከማስተዋወቅ አልፈው የአንድን ሀገር ኢኮኖሚ ይደግፋሉ። ታሪኳ ከጦርነት እና ከችጋር ጋር የሚነሳው ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀደምት የሰው ልጅ መገኛ ስለመሆኗ ድንቅነሸ ወይም ሉሲ ተጠቃሽ ምሥክር ናት። የቀደምት ሥልጣኔ ማሳያም ካስፈለገ ከአክሱም የዛጉየ፣ የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የጎንደር ቤተ መንግሥታትና አብያተ ክርስትያናት ሁሉም የቀደሙ ኢትዮጵያውያን ሥልጣኔና ድንቅ የኪነ-ሕንጻ ክህሎት ማሳያዎች ናቸው። ያም ሆኖ የሀገር ወገን ወዳድ አባቶቻችን ውርስ የሆኑ ቅርሶቻችን አምሳያ ሥራ መሥራት ቢሳነን የተረከብናቸውን ቅርሶች ለተከታይ ትውልድ ለማስተላለፍ አስፈላጊውን ልዩ ጥንቃቄና እድሳት ስለማናደርግላቸው ቅርሶቻችን የመፈራረስ አደጋ ገጥሟቸዋል።

 ላለፉት በርካታ ዓመታት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመቶ ዓመታትት ወዲህ የሀገር ቅርስ ናቸው ተብለው ተመርጠው ልዩ እንክብካቤ ወፋፍራም በጀት እየተበጀላቸው ታድሰዋል። በአንጻሩ ጥንታዊ የላሊበላን አብያተ ክርስቲያናት ጨምር የጎንደር ቤተ-መንግሥታት የመንግሥት ትኩረት ተነፍጓቸው ለከፋ የመፈራረስ አደጋ ተጋልጠዋል። ጥንታዊ ቅርሶቻችን  ከዘመነ ወያኔ ጀምሮ የብልጽግና ፖለቲከኞች ለአንድ ሰሞን ዲስኩር ማሳመሪያ የሚገለገሉባቸው ቅርሶች ከመሆን ባለፈ መጠገን ቀርቶ ለቅርስ አሳቢና ተቆርቋሪ ሹሞችም መመደብ አልተቻለምና ቅርሶች በከፋ ይዞታ ላይ ወድቀዋል።

 ዛሬ የፋሲል ቤተ – መንግሥት እድሳት ጉዳይ ሲነሳ እድሳቱን ለፖለቲካ ፍጆታ ጥቅም እያዋሉት የሚገኙት የብልጽግና ሹማምንት እድሜ የተጫነው ቅርስ በጊዜና በወቅቱ እንዲታደስ ቀርቶ የነበረው ጉዳት እንዳያገኘው የሰሩት ሥራ የለም። ይልቁንም ቅርሶቹን ሊጎዱ የሚችሉትን የድምፅ እና የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የማስቆም ሥራ፣ በቤተ-መንግሥቱ ቅጥር ግቢ ሰርግ፣ የሙዚቃ ክሊፕ መሥራት፣ ለከተማው፣ ለክልል እና ለፌደራል ኃላፊዎች ክብር የሚዘጋጁ ድግሶች በሕንጻው ከፍተኛ ንዝረት የሚፈጥሩ የተለያዩ ድግሶችን ጭፈራዎች በማድረግ ቅርሶቹን አደጋ ላይ ጥለዋቸዋል። በፖለቲካ አመለካከታቸው ቅርስና ቱሪዝም ኃላፊነት የሚሰጣቸው ወገንች ጥንታዊ ቅርሶች በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ተወረው ሲጎዱና ደብዛቸው ሲጠፋ እንኳ አንዳችም የሚያደርጉት የቅርስ ማስጠበቅ የመከላከል ሥራ አላየንም። ከጎንደር ከተማ አስተዳደር እስከ ክልልና ፌደራል የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ኃላፊዎች ለቅርሶቹ ደኅንነት ብለው የሚያወጧቸውን የይስሙላ ሕግና ደንቦች እንኳ ማስፈጸም ተስኗቸዋል። የቅርስ ባለሙያዎች ለቅርስ ተቆርቋሪ ወገኖች ቤተ-መንግሥቱ አስፈላጊው ጥገና እና እንክብቤ ይደረግለት፣ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ አግባብነት በጎደለው አጠቃቀም አደጋ ላይ ነው በሚል እንደ ማንቂያ ደወል የሚሆን ጥቆማና አስተያየት እየሰነዘሩ ቢመክሩም ሰሚ አላገኙም። በኢትዮጵያ የሥልጣኔ አኩሪ የሥነ ሕንጻ ክህሎትን፣ ታሪክን ለትውልድ አሻግረው የሚሳዩ ትውልድ የሚኮራባቸው የአባቶቻችን አሻራ ቅርሶቻችን የሕልውና አደጋ ውስጥ መሆኑን እያወቅን ዝምታን መርጠናል።

   ግማሽ ክፍለ ዘመን ለሚጠጋው ጊዜ በዓለም አቀፍ ቅርስ ጥበቃ በዩኒስኮ የተመዘገቡት የጎንደር ጥንታዊ ቤተ መንግሥታቱን ጨምሮ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያን ቅርሶቻችን የ16ኛው ክ/ዘመን ኢትዮጵያውያን ጥበብና ክህሎት ይገለጥባቸዋል። የዐፄ ሱስንዮስ ቤተ መንግሥትን ጨምሮ፣ በልጃቸው ዓለም ሰገድ ፋሲል ልጆችና የልጅ ልጆች በአእላፍ ሰገድ ዮሐንስ፣ አድያም ሰገድ ኢያሱ፣ አድባር ሰገድ ዳዊት፣ መሲህ ሰገድ በካፋ፣ እቴጌ ምንትዋብ፣ ቋረኛው ኢያሱ የተገነቡት ቤተ መንግሥትና አብያተ ክርቲያናትን የቀደምት ሥልጣኔያችን ሕያው ማሳያ ኾነው ዘመን ተገፍቷል። የዓለም ቅርስ ጥበቃ እውቅና የሰጣቸው ጥንታዊ ቅርሶቻችን የዛሬ ይዞታ ምን ላይ ነው ብሎ ለጠየቀ አደጋ ላይ መሆናቸውን እንረዳለን።

ከ400 ዓመታት በላይ እድሜን ያስቆጠሩት እኒሁ ቅርሶቻችን በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያውያንን እጹብ ድንቅ የኪነ ሕንጻ ጥበብ ጋር የዘመኑን ሥልጣኔ ልክ የሚነበብባቸው የታሪክ አሻራዎቻችን ናቸው። በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ዘመናዊ የእንግዳ መቀበያ አዳራሾች፣ የሴቶች ማስዋቢያ ወሸባ ግንብ፣ እደ ጥበብ ማስተማሪያና ማሰልጠኛ ፈታይ ግንብ፣ የመጻሕፍት ቤት፣ የመንፈሳዊ ትምህርትና የሀገር ባህል ዜማ የሚሰለጥንባቸው ሰፋፊ አዳራሾች፣ የአንበሳ ቤት፣ በወቅቱ ትራንስፖርት ኹነኛ መገልገያ የነበረው የፈረስ ዘመናዊ ማቆሚያ በወግና በሥርዓት ለዛሬው ትውልድ በክብር ተላልፎልናል። ዳሩ ግን ያለ በቂ ጥናት የሚካሄዱ ጥገናዎች በቅርሱ ላይ ችግር፣ ቅርሱም ላይ አደጋን ሲያስከትሉ ተመልክቻለሁ። ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ትኩረት አላገኘምና ከጊዜ ወደ ጊዜ የቅርሶቹ ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነ በባለሙያዎች የሚጠቀሱት አደጋዎች መጠነ ሰፊ ናቸው።

  በቅርሱ ጣርያ ላይ ከሚታዩ ችግሮች በተጨማሪ ግድግዳዎች ተሰነጣጥቀው ነበር። የመንሸራተትና የመዝመም እክሎችም ገጥመውት ነበር። በአእዋፋትና በእጽዋት ንክኪ የተነሳ ተሸርሽሮም ነበር። ካቦቹም ወዳድቀው የጥገና ሥራ በመሠራቱ ከዚህ በፊት የተሻለ ሁኔታ ላይ ቢገኙም በቂ አይደለም ብለዋል።

    ዛሬ የፋሲል ቤተ – መንግሥት እድሳት ጉዳይ ሲነሳ እድሳቱን ለፖለቲካ ፍጆታ ጥቅም እያዋሉት የሚገኙት የብልጽግና ሹማምንት እድሜ የተጫነው ቅርስ በጊዜና በወቅቱ እንዲታደስ ቀርቶ የነበረው ጉዳት እንዳያገኘው የሰሩት ሥራ የለም። ይልቁንም ቅርሶቹን ሊጎዱ የሚችሉትን የድምፅ እና የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ የማስቆም ሥራ፣ በቤተ-መንግሥቱ ቅጥር ግቢ  ሰርግ፣ የሙዚቃ ክሊፕ መሥራት፣ ለከተማው፣ ለክልል እና ለፌደራል ኃላፊዎች ክብር የሚዘጋጁ ድግሶች በሕንጻው ከፍተኛ ንዝረት የሚፈጥሩ የተለያዩ ድግሶችን ጭፈራዎች በማድረግ ለቅርሶች አደጋ ሲወድቁ ተመልካች የሆኑት ቅርስና ቱሪዝም የፖለቲካ ሹም ኃላፊዎች ጥንታዊ ቅርሶች በሕገ ወጥ የመሬት ወረራ ተወረው ሲጎዱና ድብዛቸው ሲጠፋ አንዳችም የተደረገ የቅርስ ማስጠበቅ የመከላከል ሥራ የለም።  

  ከጎንደር ከተማ አስተዳደር እስከ ክልልና ፌደራል የቅርስ ጥበቃና ቱሪዝም ኃላፊ ተብየዎች ለቅርሶቹ ደኅንነት ብለው የሚያወጧቸውን የይስሙላ ሕግና ደንቦች እንኳ ማስፈጸም ተስኗቸዋል። የቅርስ ባለሙያዎች ለቅርስ ተቆርቋሪ ወገኖች ቤተ-መንግሥቱ አስፈላጊው ጥገና እና እንክብቤ  ይደረግለት ፣ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ አግብነት በየጎደለው አጠቃቀም አደጋ ላይ ነው በሚል እንደ ማንቂያ ደወል የሚሆን እየጠቆሙ ቢመክሩም ሰሚ አላገኙም። በኢትዮጵያ የሥልጣኔ አኩሪ የሥነ ሕንጻ ክህሎት እያሳዩ ታሪክ ለትውልድ አሻግረው የሚሳዩን ትውልድ የሚኮራበት የአባቶቻችን አሻራ ቅርሶቻችን የሕልውና አደጋ ውስጥ መሆኑን እያወቅን ዝምታን መርጠናል።

የፖለቲካ ሹሞች አደንቋሪ ዲስኩር

  ስለ ፋሲል ቤተ መንግሥት በአደጋ ላይ መውደቅ የጎንደር ከተማ እና የክልል ባሕልና ቅርስ ሹሞች ሲጠየቁ ‹‹ለችግሮቹ ዋናው ምክንያት ለቅርሶቹ ሳይንሳዊ እና በጥናት ላይ የተመሠረተ ጥገና እና እንክብካቤ አለመደረጉ ነው ይላሉ›› ብለው ይመልሳሉ። በአንጻሩ የኢትዮጵያ የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ 9ኙን የጎንደር አብያተ መንግሥታት የሚያካትት ጥናት እንደተጀመረ በመጠቆም   “…ደረጃውን የጠበቀ ሳይንሳዊ ጥገና ለማድረግ በጀት ተመድቧል፣ ሥራው ይጀመራል” ሲሉን  ዳይሬክተሩ 35 ሚሊዮን ብር መፈቀዱና 25 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ በጀት ለጎንደር አብያተ መንግሥታት ጥገና የሚውል ነው” ካሉን ዓመት ተገባዷል። የጥናቱ ሁለት ዐበይት ክፍሎችን የነገሩን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የኢንጅነሪንግ ዘርፉን ኤም ኤች ኢንጅነሪንግ እና የአርክቲክቸሩን ዘርፍ ደግሞ ፋሲል ጊዮርጊስ አርክቲክቸር እንዲይዙት ተደርጓል ብለውንም ነበር። ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው ቃል ግን የተጨበጠ አልሆነም። እነሆ ወራትና ዓመታት ገፍተን ይሆናል ያሉን የሆነም ሆነ የተሰራ ጥገናም ሆነ እድሳት መሬት ላይ አልታየም። አለመታደል ሆኖ የፋሲለደስ ቤተ መንግሥት ዛሬም ፖለቲካ ሆኗልና ባለሥልጣኑ በአደባባይ የሰጡን ሁሉ መረጃ ዛሬ ላይ ከዲስኩር ያለፈ መሆን አልቻለም ።

በባለሙያዎች የሚጠቆሙት በቅርሱ ላይ ያንዣበበ አደጋ

* የዳዊት ቤተ-መንግሥት፣ የዐፄ ባካፋ ቤተ-መንግሥት የምንትዋብ ቤተ-መንግሥት ሕንጻዎች ስንጥቅ የተመለከቱ የቅርስ ባለሙያዎች ባንድ ወቅት በስንጥቁ ላይ ያሰሩት የስንጥቅ አደጋ መለያ ከልክ አልፎ እንደተበጠሰ ተመልክቻለሁ። ምልክቱ ሲታሰር ከአንድና ከሁለት ሴንቲ ሜትር ይለካ የነበረው ስንጥቅ አሁን ወደ 5 እስከ 6 ሴንቲ ሜትር በላይ እየሰፋ ሄዷል።

* በምስጥና በፈንገስ ምክንያት የዐፄ ፋሲል ዋናው ሠገነቶች እንጨት በምስጥ ተበልቶ፣ በዝናብ  እየበሰበሰ ከፈራረሰ ዓመታት ተቆጥረዋል። በተደጋጋሚ አስፈላጊው ጥገና ይደረግ ብለን ብንጠይቅም የቤተ መንግሥቱ ሰገነቶችም ሆነ የሕንጻው የመደርመስ አደጋ የዐፄዎቹ ራት እያሉ ጥምቀት በመጣ ቁጥር የሚያደነቁሩንን የፖለቲካ ሹሞችን ቀልብ አልሳበም።

*  ከቤተ መንግሥቱ የቅርብ ርቀት በሚገኘው የመስቀል አደባባይ በሚደረጉ የተለያዩ ስብሰባዎች፣ ባዛሮችና የሙዚቃ ዝግጅቶች የሚለቀቁ የሞንታርቦ ከፍተኛ ድምጾችና ግርግርን ቅርሱን ለአደጋ ዳርጎታል፡፡

* በቤተ መንግሥቱ የቅርብ ርቀት በሚገኘው አውራ መንገድ የሚተላለፍ የከባድ መኪና ንዝረት  ቅርሶቹ እንደሰነጠቁና ለመፍረስ አደጋ እንዲጋለጡ ምክንያት ሆኗዋል።

* የዐፄ ፋሲልና የቀሩት ነገሥታት ቤተ መንግሥት ሕንጻዎችና አብያተ ክርስቲያናትን ከአደጋ ለመታደግ የየቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ከ20 ሚሊይን ብር በላይ በጀት አስመድቤያለሁ ቢልም ተቋሙ በቋሚነት ለመደበው ከ1 ሚሊዮን ብር በጀት ምን እንደተሰራበት ነግሮን አያውቅም።   

 ዛሬስ ምን እየሆነ ነው?

ለሁለት ምዕተ አመት የኢትዮጵያ መናገሻ ሆና ያገለገለችው ጥንታዊዋ ጎንደር እና በዓለም ቅርስነት በዩኒስኮ የተመዘገቡት ጥንታዊ የፋሲል ቤተ – መንግሥትና አብያተ ክርቲያናት ቅርሶች ጉዳይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጉብኝት በኋላ ሌላ መልክ ይዟል። እርግጥ ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ጉብኝት ታሪካዊ ጥንታዊ ቅርሶቻችን ለዓመታት የተነፈጋቸውን ትኩረት ማግኘታቸው ባይከፋም ግልጽነት ባልታየበት እየተካሔደ ያለው የፋሲለደስን ግቢ የማሳመር አሠራርና ሒደት ጅማሮ በባለ ሙያዎች ቅሬታ እየተሰማበት ይገኛል። ለሀገራችን ቱሪዝም መስሕብ የሆኑት የጎንደር ጥንታዊ ቤተ-መንግሥትና አብያተ ክርስቲያናት ባለፉት ሦስትና አራት ዓመታት ጥገናና እድሳት ስላልተደረገላቸው ከፍ ወዳለ አደጋ ላይ መውደቃቸው እየታወቀ መንግሥት ለማስዋብ ሥራው ከመሐል አዲስ አበባ ባለሙያዎቹን ወደ በቦታው መመደቡ ከጋሪው ፈረሱ የመቅደም ጉዳይ ሆኗል ሲሉ መረጃውን ያቀበሉኝ ወገኖች ጥቆማ ብዕር አነሳ ዘንድ ምክንያት ሆኖኛል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን የቅርሶች ጉብኝት በኋላ በአደጋ ላይ የወደቀው የፋሲል ቤተ መንግሥት ጥገናና እድሳት ጉዳይ እንደ አዲስ መነጋገሪያና አጀንዳ ከመሆን አልፎ ባለሙያዎች ከመመደብ አልፎ ከፋሲል ቤተ-መንግሥት ቅጽር ግቢ ውስጥ የነቀረው የቅርስ ጥበቃ ቢሮ ከቀናት በፊት ግቢውን እንዲለቁ ተደርገዋል። ዓለም አቀፉ የቅርስ ጥበቃ ድርጅትና የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ባለሙያዎችን ተመልካች ከመሆን ባለፈ በሥራው ባልተካተቱበት ጥናትና የሥራ ጅማሬ ግልጽ መረጃ ባይኖርም ለተከታታይ ወራት የፋሲል ቤተ-መንግሥት ለጎብኝዎች እንደሚዘጋ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል።

   የጎንደር ቤተ-መንግሥትና አብያተ ክርስቲያን እድሳት ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው ቅርሶች እንደመሆናቸው የዓለም ሀብት ጭምር ናቸው። ጥንታዊ ቅርሶች ሲታደሱ ጥንታዊ ይዘታቸውን እንዳይስቱ የዓለም አቀፍ ቅርስ ጥበቃና ከክልል እስከ ፌደራል የቅርስ እድሳት ባለሙያዎች ተሳትፎ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል የተገባው የቅርስ ማደሻ ስጦታም ሆነ ከቅርስ ጥበቃ ባለሥልጣን ለቅርሱ እደሳ አስፈላጊው በጀት ከተገኘ ቅርሱን ከተጋረጠበት አደጋ ለመከላከል ጥገናውንና እድሳቱ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ይላሉ።

 በአደጋ ላይ ስላለው እድሳት ሊደረግለት ጥናት መጀመሩን መረጃ በደረሰኝ የጎንደር ቤተ-መንግሥት ቅርስ ጉዳይ ዘርዘር ያለ መረጃዎችን እስከ ማስረጃው በቀጣይ ዳሰሳየ የምመለስበት ይሆናል።

ቸር ይግጠመን

ይቀጥላል…

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ፤ አደረሰን

ሰማያት ተከፈቱ ፣ ምስጢርም ተገለጠ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘመዷ ቅድስት...

አባቴ ለእኔ አባት ብቻ አልነበረም፤ ለእናቴ ታማኝ ባል፣ ለሁላችንም ደግሞ የደስታ ምንጭ ነበር

"አባዬ… ዛሬ ላለሁበት ማንነት መሰረት የሆንከኝ አንተ ነህ!" ​የአርቲስት...

የአንበሶቹ ትንሳኤ፦ የዳካር እንባ እና የቴራንጋ ድል

​በዳካር ሰማይ ስር ዛሬ ጨረቃ አልወጣችም፤ ይልቁንም በሚሊዮን የሚቆጠሩ...

የጥምቀት በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት እየተከበረ ነው

የጥምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት...