ትራምፕ ኢራን ያበለጸገችውን ዩራኒየም ማስወገድ ”ረዥም እና አስቸጋሪ” ሂደት ነው አሉ

Date:

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ ከኢራን የበለጸገውን ዩራኒየም ማውጣት ከባድ መሆኑን በማኅበራዊ ሚደያ ገጻቸው ላይ ተናገሩ።

“ዘመቻ ሚድናየት ሃመር የተሟላ እና ሙሉ በሙሉ የኢራንን አቧራማ የኒውክሌር ተቋማት ያወደመ ነበር። ስለዚህ ቆፍሮ ማውጣት ረዥም እና አስቸጋሪ ሂደት ነው” ሲሉ ጽፈዋል።

ዘመቻ ሚድ ናይት ሐመር አሜሪካ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር በኢራን ላይ የፈጸመችው ድብደባ መጠሪያ ሲሆን 125 የአሜሪካ ጦር አውሮፕላኖች ተሳትፈውበታል።

የአሜሪካ ጦር አውሮፕላኖች የደበደቧቸው ሦስት የኢራን የኒውክሌር ተቋማት ፎርዶ፣ ናታንዝ እና ኢስፋሃን ናቸው።

ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ልጥፋቸው ላይ “ሐሰተኛው ሲኤንኤን እና ሌሎች ብልሹ የመገናኛ ብዙኃኖች የጦር አውሮፕላን አብራሪዎቻችን የሚገባቸውን ክብር ሳይሰጧቸው ቀርተዋል፤ ሁልጊዜም ማንኳሰስ እና ማንቋሸሽ- ተሸናፊዎች።”

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...