አየር መንገዱ 6 ዘመናዊ ድሪም ላይነር አውሮፕላኖችን ሊገዛ ነው

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስድስት ዘመናዊ ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል።

አየር መንገዱ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ከኩባንያው ጋር ያደረገው ግዙፍ ስምምነት የአየር ላይ የበላይነቱን ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል።

የአውሮፕላኖቹ ግዢ ከአዲስ አበባ ወደ አውሮፓ፣ እስያና ሰሜን አሜሪካ የሚደረጉ አህጉር አቋራጭ በረራዎችን ይበልጥ ምቹና ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

አውሮፕላኖቹ በነዳጅ ቆጣቢነታቸው እና በጭነት አገልግሎት ውጤታማነታቸው ተመራጭ እንደሆኑም ተገልጿል።

ይህ ግዢ አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ያለውን ግዙፍ የድሪምላይነር ስብስብ ይበልጥ የሚያጠናክርለት ይሆናል ተብሏል።

አየር መንገዱ እንዲህ ያሉ ግዙፍ ኢንቨስትመንቶች ውስጥ መግባቱ በ2035 በዓለም ቀዳሚ ከሆኑ 20 አየር መንገዶች ተርታ ለመሰለፍ የያዘውን ግብ እንደሚያፋጥነው ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...