ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

Date:

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለውጭ ተቋም የሚሰጠውን የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ለናይጄሪያው የፋይናንስ ግዙፍ ተቋም ‘ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ’ መስጠቱን በይፋ አስታወቀ።

​ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የተሰጠው ይህ ፈቃድ፤ ባለሥልጣኑ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና ሌሎች የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ለወራት ያደረጉትን ጥብቅ የሕግና የሰነድ ምርመራ ተከትሎ የተሰጠ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክር ሀና ተኸልኩ በተለይ ለካፒታል ጋዜጣ ተናግረዋል።

ዩናይትድ ካፒታል ‘ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር’ የተሰኘ ሙሉ በሙሉ የራሱ የሆነ የአካባቢው ቅርንጫፍ በመክፈት ከስድስት አስርት ዓመታት በላይ ያካበተውን የአፍሪካ አቀፍ ልምድ ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ገብቷል።

​ባለስልጣኑ እንደገለፀው ፤ ይህ ሙሉ በሙሉ በውጭ ተቋም ባለቤትነት የተያዘ ፈቃድ መሰጠቱ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሊበራላይዜሽን ማሻሻያ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ማረጋገጫ ነው።

ተቋሙ በሕግ ከተቀመጠው የ25 ሚሊዮን ብር አነስተኛ ካፒታል በላይ፣ ከ1.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ በቀጥታ ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

የቅዱስነታቸው በዓለ ዕረፍት በሶዶ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳም ተከበረ !

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሦስተኛ ፓትርያርክ የነበሩት ብፁዕ...