አስተዳደሩ የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ እንደሚመለስ ማረጋገጫ ሰጠ

Date:

ከንቲባዋ በማኀበራዊ ገፃቸው እንዳሰፈሩት
“የላቀ የጤና አገልግሎት ለሀገር ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በየደረጃው ሲካሄድ የነበረው የጤና ባለሙያዎች ውይይት የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል።

መድረኩ የጤና ባለሙያዎች ለሀገር ግንባታ ያላቸውን ሚና በመረዳት በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ፣ ለሀገረ ግንባታ በጋራ መቆምን ፣ የተሻለ አገልግሎት መስጠት በሚቻልበት መንገድ ላይ ለመምከር እና ከባለሙያዎቹ የሚነሱ ጥያቄዎችን እና ሃሳቦችን በማዳመጥ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ነው::

የጤና ባለሙያዎቹ በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች እና የተገነቡ መሰረተ ልማቶች ጤናማነቱ የተጠበቀ ማኅበረሰብን ለመፍጠር እንዲሁም በሽታዎችን ለመከላከል አጋዥ መሆናቸዉን ያነሱ ሲሆን ፤ በጤና ሴክተር ላይ እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጪ እና የሁሉን ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን በሚገባዉ ላይም ተግባብተናል።

በቀጣይ የጤና ሴክተሩን ደረጃ ይበልጥ ለማሳደግ ፤ ነባር የጤና ተቋማት ለማሻሻል፣ ከተማችንን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመሩ አዳዲስና ዘመናዊ የጤና ተቋማትን ግንባታ ማጠናቀቅ፣ ብቁ የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት፣ ወቅቱ የደረሰበት ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች ማሟላት እንዲሁም የጤና ባለሙያዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሰረታዊ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን የምንሰራ ይሆናል::

የጤና ባለሙያዎቹ በርከት ያሉ የጥቅማጥቅም እና የደሞዝ ማሻሻያ ጥያቄዎችን እና ሃሳቦችን ያነሱ ሲሆን አገልግሎትን የሚመጥን ጥቅማጥቅም አለመኖሩን በመገንዘብ እየተሰራ ባለዉ በጤና ሪፎርም ጥናት ላይ በመመስረት በአጭር ፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ምላሽ የሚሰጥ መሆኑን አምነንበታል።

በከተማ አስተዳደሩ አቅም የሚፈቱትን የትርንስፓራት አገልግሎታ ፣በማህበር ተደራጅቶ የመኖሪያ ቤት መገንባትን ፣ ነፃ የህክምና አገልግሎት፣ የትርፍ ሰዓት ክፍያን መመሪያ በተሟላ ሁኔታ መተግበርን ጨምሮ አስተዳደሩ በአጭር እና በመካከለኛ ጊዜ እቅድ ምላሽ ለመስጠት ተግባብተናል::
በመጨረሻም ያሏቸዉን ጥያቄዎች ቢሆን እያገለገሉ የሚጠይቁት እንጂ ከሙያዊ ስነምግባር ዉጪ ስራ አቁመዉ የሚጠይቁት አለመሆኑን አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...