አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በካናዳ ሀገር ሊሸለሙ ነው

Date:

የሰንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መስራችና ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል ታፈሰ በንግዱ ዘርፍ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋፅኦ እና ለበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸው በካናዳ የሚሰጠውን የ“ቢቂላ ሽልማት” ሊሸለሙ ነው።

ባለሀብቱ ከምንም ተነስተው በኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፍ የቢዝነስ ተቋም መገንባት በመቻላቸው ለዚህ ክብር የበቁ ሲሆን በመጪው መስከረም 28 ቀን 2026 ዓ.ም በቶሮንቶ ከተማ በሚካሄደው ደማቅ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ በአካል ተገኝተው ዕውቅናቸውን የሚረከቡ ይሆናል።

​ዘንድሮ 12ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን የሚያከብረውና በካናዳ ነዋሪ በሆኑ ኢትዮጵያውያን የተመሠረተው የቢቂላ ሽልማት ተቋም በትምህርት፣ በንግድ፣ በሙያና በማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፎች የላቀ ስኬት ያስመዘገቡ አርአያዎችን በየዓመቱ ይሸልማል።

በዘንድሮው መርሃ ግብር ላይ ከአቶ ሳሙኤል በተጨማሪ አዶናይ ብርሃኔ፣ አና ጌታነህ፣ ዶክተር ምህረት ደበበ እና አቶ ግዛው በቀለ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ዕውቅና የሚያገኙ ሲሆን ታዋቂው ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ደግሞ የዕድሜ ልክ የክብር ሽልማት ተበርካች ይሆናሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር በዓለም የምግብ ምርምር ድርጅት ሹመት ተሰጣቸው

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአግራ (AGRA) የቦርድ ሰብሳቢ...

በምክክሩ ወቅት በሀሳብ ልዩነት “አድማ የመቱ” ነበሩ

ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በ22ኛው ቀን ውሎው በስልታዊ ቡድን ደረጃ...

በፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል ያለዉ ግጭት እንዳሳሰበው የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን ገለፀ

የአውሮፓ ሰላም ፋውንዴሽን  በኢትዮጵያ ፌደራላዊ  መንግሥት እና በህዝባዊ ወያኔ...

የብሔራዊ ትያትር ሕንፃ ግራጫ ቀለም የጥበብ ማዕከል መገለጫ አይሆንም

ከሥር ከላይ በስተግራ የምታየው ፎቶ 1 የታሪካዊዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...