ትርፉ ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት አኳያ ሲተያይ የ11.8 ቢሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2025/26 የሂሣብ ዓመት የባንኩ ጠቅላላ ገቢ 85.37 ቢሊዮን ብር ደርሷል፣ የባንኩ ጠቅላላ ወጪ ደግሞ 44.62 ቢሊዮን ብር መሆኑ ተነግሯል፡፡
አዋሽ ባንክ የ2025/26 ሂሣብ ዓመትን በማስመልከት ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ፀሃይ ሽፈራሁ መግለጫ ሰጥተዋል።
የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ብር 622 ቢሊዮን ብር ደርሷል ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የባንኩን የተከፈለ ካፒታል አምና ከነበረበት 27.9 ቢሊዮን ብር የ38 በመቶ እድገት በማሳየት 38.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል ተብሏል፡፡
የባንኩ ጠቅላላ ተቀማጭ 467.8 ቢሊዮን ብር ደርሷል፣ ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት አንጻር የ41 በመቶ ወይም የብር 135 ቢሊዮን ጭማሪ አሣይቷል ይላል የባንኩ ሪፖርት፡፡
ባንኩ በበጀት ዓመቱ 2.65 ቢሊዮን ዶላር የውጪ ምንዛሬ ማግኘቱን የጠቀሰ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ635 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል ብሏል።
ባንኩ በአዋሽ ለሁሉም፤ በጥላ እና በእርፍ የዲጂታል አማራጮች ከ1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞቹ ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩ ተጠቅሷል።
አዋሽ ባንክ በጎርቤት ሀገር ቅርንጫፍ ለመክፈት ለሀገሪቱ ብሔራዊ ባንክ ጥያቄ ማቅረቡን የተናገሩት ዋና ስሰፈራ አስፈፃሚው የሀገሩ ስም ከመጥቀስ ግን ተቆጥበዋል
ባንኩ የበጀት አመቱን ያጠናቀቀው በዋና ዋና አመላካቾች ከፍተኛ ስኬት በማስመዝገብ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚ የባንኩ አክሲዮኖች በኢትዮጵያ ሰነደ ሙአለነዋይ ገበያ መመዝገቡን ተከትሎ ከፍተኛ ተፈላጊ መሆን መቻሉን ጠቅሰዋል።
ሸገር 102.1
