ኢራን ሆርሙዝ እንዲከፈት እና የኒውክሌር ንግግር እንዲዘገይ የሚጠይቅ እቅድ ለአሜሪካ ማቅረቧ ተዘገበ

Date:

ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት እና ጦርነቱ እንዲቋጭ፤ የኒውክሌር ጉዳይ ግን በስምምነቱ ቀጣይ ደረጃ ንግግር እንዲደረግበት የሚጠይቅ የሰላም እቅድ ማቅረቧን የአሜሪካው የዜና ምንጭ አክሲዮስ ዘገበ።

አክሲዮስ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣንን እና ከጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ እንደሚያስረዳው፤ ኢራን እቅዱን ያቀረበችው በአሸማጋይዋ ፓኪስታን በኩል ነው።

እቅዱ በዋነኛነት የሚያተኩረው ከሁሉም በፊት በሆርሙዝ ወሽመጥ እና አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ ጉዞዎች ላይ በጣለችው እገዳ ምክንያት ለተፈጠረው ቀውስ መፍትሔ ማበጀት ላይ ነው።

በዚህም መሠረት የተኩስ አቁሙ ለረጅም ጊዜ እንዲራዘም ወይም ሁለቱ አገራት በቋሚነት ጦርነት ለማቆም እንዲስማሙ የሚጠይቅ ሀሳብ እቅዱ ውስጥ መካተቱን ዘገባው ጠቅሷል።

በኢራን እቅድ መሠረት የኒውክሌር ድርድር የሚጀመረው የሆርሙዝ ወሽመጥ ከተከፈተ እና የአሜሪካ እገድ ከተነሳ በኋላ ነው።ዋይት ሀውስ የኢራን እቅድ የደረሰው ሲሆን የትራምፕ አስተዳደር የኢራንን እቅድ ይመለከተው እንደሆነ አለመታወቁን አክሲዮስ ዘገቧል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ፓኪስታን ሲጓዙ ከአሜሪካ ጋር የሚደረገው ንግግር በድጋሚ ይጀምራል የሚል ተስፋን ጭሮ ነበር። አራግቺ እንደተጠበቀው ከአሜሪካ ልዑካን ጋር ባይነጋገሩም ስለ ሰላም ድርድር ማንሳታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

አክሲዮስ እንዳስነበበው ከሆነ፤ አራግቺ በኢስላማባድ ቆይታቸው የኒውክሌር ጉዳይን ወደ ጎን የማድረግ ሀሳብን አንስተዋል።

አክሲዮስ ያነጋገራቸው አንድ ምንጭ የአሜሪካ ጥያቄ የሚመለስበትን መንገድ በተመለከተ በኢራን አመራር መካከል ስምምነት አለመኖሩን አራግቺ ለፓኪስታን፣ ግብጽ፣ ቱርክ እና ኳታር አሸማጋዮች መናገራቸው ገልጸዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ከኢራን ጋር ለሚደረግ ድርድር ልዑካኖቻቸውን እንደማይልኩ እና በስልክ ንግግር ማድረግ እንደሚቻል ተናግረዋል።

BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 2ኛ የወርቅ ሜዳሊያ አገኝች

በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የተወዳደሩት  ዮርዳኖስ ጽጋብ እና ሽቶ...

“አዳም አንድ ደራሲ የሚያስፈልጉት ሁሉም ግብዓቶች ተሟልተው ያሉት ፀሐፊ ነው”

አዳም ረታ ሥራዎቹን ለአንባቢ ማድረስ የጀመረው ከ1970ዎቹ አንስቶ ነው።...

ከፍተኛ የግብር ክፍያ በሕጋዊ ነጋዴው ላይ በመጫን ሲፈጽሙት …

መንግስት ከግብር የሚያገኘው ገቢ የቀነሰው ወይም ከሀገር ውስጥ አጠቃላይ...

ሆስፒታሊቲ እና ቱሪዝም እውቅና እና ሽልማት መርሃ-ግብር ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ባለሙያዎች ማኅበር ሁለተኛውን የሆስፒታሊቲ...