እቅዱ 4 ሺህ 800 የከተማ እና ሀገር አቋራጭ የኤሌክትሪክ ባሶችን ማሠማራት እንደሚያካትት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አስታውቋል፡፡
ስለ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ውጥኖች ሌሎች መርጃዎች፦
➖ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ብቻ ከ110 ሺህ በላይ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የሚንቀሳቀሱ ሲሆን ከ90 በላይ የኤሌትሪክ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች አሉ፡፡
➖ መዲናዋ ብቻ 1 ሺህ 176 የኤሌትሪክ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች ያስፈልጓታል።
➖ በአዲስ አበባ በሁለተኛው የማስፋፊያ ምዕራፍ 54 ተጨማሪ ኤሌትሪክ ኃይል መሙያዎች ይገነባሉ።
➖ ከአዲስ አበባ ውጭ ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ድሬዳዋና ጅግጅጋ የኃይል መሙያ ጣቢያዎችን መትከል ጀምረዋል።
👉 የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ትራንስፖርት ስትራቴጂ የካርበን ልቀትን 20 በመቶ ለመቀነስ ወጥኗል፡፡
