“ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ በፈለገችውመንገድ መጠቀም ትችላለች”

Date:

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አብዲራህማን ዳሂግ ሀገራቸው በባሕር በር ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ለመተባበር አሁንም ሙሉ ዝግጁነት እንዳላት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር የማግኘት መብት እንዳላት ሶማሊላንድ በጽኑ እንደምታምን የጠቆሙት ሚንስትሩ፣ ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ በፈለገችው መንገድ መጠቀም እንደምትችል አረጋግጠዋል።

ሆኖም ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ አግኝቻለሁ ያለችው የ19 በመቶ የባለቤትነት ድርሻ ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ ባካል ኢትዮጵያ ወደቡን በሙሉ አቅሙ እስካሁን አልተጠቀመችበትም የሚል አጭር ምላሽ መስጠታቸውን ተገልጧል።

በተጨማሪም ሚንስትር ባካል ኢትዮጵያ የሶማሊላንድን ቁልፍ አጋርነት ከግምት ውስጥ በማስገባት አንድ ቀን እውቅና እንደምትሰጣቸው እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ነገር ግን ሶማሊላንድ ይህንን እውቅና እንድታገኝ በኢትዮጵያ ላይ ምንም ዓይነት ግፊት ማድረግ እንደማትፈልግና ጉዳዩን ለራሷ ለኢትዮጵያ እንደምትተወው አስገንዝበዋል። ይህ መግለጫ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትብብር ቀጣይነት ባለው መልኩ ሊመራ እንደሚችል አመላካች ሆኗል።

ሪፖርተር

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...