ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ አባል ለመሆን የ295 ሚሊዮን ዶላር አክሲዮን ልትገዛ ነው

Date:

​የኢፌድሪ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ኢትዮጵያ የብሪክስ ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ (NDB) አባል እንድትሆን የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፅድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷል።

በዚህም መሠረት ሀገሪቱ እያንዳንዳቸው 100 ሺህ ዶላር ዋጋ ያላቸውን 2,945 አክሲዮኖች በአጠቃላይ በ295 ሚሊዮን ዶላር ለመግዛት ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ከዚህ ክፍያ ውስጥ 20 በመቶው (58.9 ሚሊዮን ዶላር) ወዲያውኑ የሚከፈል ሲሆን፣ ቀሪው በ13 ዓመታት ከግማሽ ውስጥ በ14 ተከታታይ ክፍያዎች ይፈጸማል።

​ይህ አባልነት ኢትዮጵያ አማራጭ የልማት ፈንድ እንድታገኝ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን እንድታስፋፋና ማክሮ-ኢኮኖሚዋን እንድታረጋጋ ከፍተኛ ዕድል ይፈጥራል።

በተጨማሪም በግብርና፣ በኃይል እና በታዳሽ ኢነርጂ ዘርፎች ለሚከናወኑ የቅድሚያ ፕሮጀክቶች የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

ባንኩ አባላቱ በሀገር ውስጥ ምንዛሬ እንዲገበያዩ የሚያበረታታ በመሆኑ፣ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ጫና ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጉምሩክ ኮሚሽን ከአንድ ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት 725.25 ቢሊዮን ብር...

ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር የአፍሪካ ንፁህ ኢነርጂ ፈንድ አምስቱ አቅኚ የኢትዮጵያ ድርጅቶች ተመረጡ

በምስራቅ አፍሪካ የንፁህ ኢነርጂ አቅርቦትን በማሳደግ የስራ እድልን ለመፍጠርና...

ታላቅ የምስጋና እና የስጦታ መርሃ-ግብር ጥሪ!

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ባለፉት 5 ዓመታት ላበረከቱት ከፍተኛና ታላቅ...

የቀድሞዉ የኢራን ላዕላይ መሪ አያቶላሕ ዓሊ ኻምኔይ ተቀበሩ

ዩናይትድ ስቴትስና እስራኤል ባለፈዉ የካቲት ማብቂያ ላይ የገደሏቸዉ የኢራን...