“ኢትዮጵያ ያላት የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ዕድገት አቅም የሚደነቅ ነው”

Date:

  • ጌሮልድ ሽዋርዝ

ኢትዮጵያ በቱሪዝምና በኢኮኖሚ ዕድገት ያላት አቅም የሚደነቅ ነው ሲሉ በዓለም አቀፍ የጀርመን ትብብር የሥራ ሽግግር ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ጌሮልድ ሽዋርዝ ገለጹ።

በዓለም ዓቀፍ የጀርመን ትብብር የሥራ ሽግግር ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ጌሮልድ ሽዋርዝ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ የግሉ ዘርፍ ልማት ተነሳሽነት እና በቱሪዝም ዘርፉ ኢንቨስትመንትን ማስፋፋት ወሳኝ ነው።

በቅርቡ የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አዳዲስ የቱሪስት መስህቦችን መፍጠር ገልጸዋል።

ይህም የአውሮፓና የሌሎች ሀገራት ቱሪስቶችን ለመሳብ እና የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ዕድገት ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንደሚያበረክት አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ ያሏት በርካታ ቅርሶችና የቱሪስት መደረሻ ቦታዎች ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት ትልቅ እድል እንደሚፈጥሩ ጠቁመዋል።

ዓለም ዓቀፍ የጀርመን ትብብር የሥራ ሽግግር ፕሮግራም ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ 15 ሺህ 700 ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር መቻሉን አንስተዋል።

በተጨማሪም ፕሮግራሙ በስድስት ዓመት ውስጥ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በአገልግሎት፣ በፋይናንስ እና በምርት ዘርፎች ተጨማሪ 15 ሺህ ለሚደርሱ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ማቀዱን ተናግረዋል።

@ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...