ከሕግ መንደር

Date:

ጋና ጥንቆላ” የሚያስከስስ ወንጀል መኾኑን የሚያስቀር “ሕግ ልታጸድቅ መኾኑ ተነገረ

ጥንቆላ ከሰሀራ በታች ባሉ ሀገራት በተለይም በገጠሩ ማህበረሰብ ያልተለመደ ነገር ባይኾንም ሴትዮዋ ተደብደበው የተገደሉበት መንገድ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጣ አስከትሏል። አፍሪካዊቷ ጋና ጥንቆላ በወንጀል የሚያስከስስ መሆኑን የሚያስቀር ህግ ልታጸድቅ ትችላለች ተብሏል። የጋና ፖርላማ በጥንቆላ የተከሰሱ ሰዎችን ለመከላከል የሚያስችል ረቂቅ ሕግ አጽድቋል። በሀገሪቱ በጥንቆላ የተሰማሩ ሰዎች ማህበሰሰባዊ መገለል እና ጥቃት ይደርስባቸዋል። ይህ ረቂቅ ሕግ የቀረበው በፈረንጆቹ 2020 በሳቫና ግዛት የ90 ዓመት አዛውንት ሴት በቡድን በመደብደባቸው እና ድርጊቱ በሀገሪቱ እና በዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች በመወገዙ ምክንያት መኾኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ረቂቅ አዋጁ በማህበረሱ የተገለሉ ጠንቋዮች የሚኖሩበት መጠለያም እንዲፈርስ ያዛል። ሕጉ ተግባራዊ እንዲኾን የጋናው ፕሬዝደንት ናኖ አኩፎ ማጽደቅ ይኖርባቸዋል።

ድንቃይ

ጃፓን ሰራተኞች ቆመው የሚተኙባቸውን አልጋዎች በምግብ ቤቶች መግጠም ጀመረች

እስያዊቷ ሀገር ጃፓን ለረጅም ሰዓት በስራ የደከሙ ዜጎቿ አጭር እረፍት የሚያደርጉባቸውን አልጋዎች በየምግብ ቤቶቹ እየገጠመች ነው። ጃፓን ለረጅም ሰዓት በሚሰሩ ሰራተኞቿ ትታወቃለች። ይህ ለረጅም ስአት ያለእረፍት የመስራት ባህል ሀገሪቱን ፈጣን እድገት እንድታስመዘግብ ቢያደርጋትም ችግር ማስከተሉ አልቀረም። ቶኪዮ ከ1970ዎቹ ወዲህ ሀገሬው “ካሮሺ” በሚለው የማህበራዊ ችግር ውስጥ ወድቃለች። የዓለም ጤና ድርጅት ጥናት እንደሚያሳየው በጃፓን በእንቅልፍ ማጣት በየዓመቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጤናቸው ተቃውሶ ሕይወታቸው እያለፈ ነው። ይህን ችግር ለመፍታት ያለመው ኮዮጁ ፕላይውድ ኮርፖሬሽን የተባለው ኩባንያ ዜጎች ለአጭር ጊዜ የሚተኙባቸውን አልጋዎች በየምግብ ቤቶቹ መግጠም መጀመሩም የእረፍት ማጣት ቀውሱን ያሳያል ተብሏል። አልጋዎቹ በተለምዷዊው መንገድ ቢሰሩ ቦታ ስለሚይዙ አግድም ሳይሆን ሽቅብ የሚቆሙ ተደርገው ተሰርተዋል። በአልጋዎቹ የሚተኙት ሰዎች የማንቂያ ደወል (አላርም) ሞልተው በምቾት አጭር እንቅልፍ (ናፕ) ይተኛሉ የሚለው “ጂራፍናፕ” የተባለው መኝታ አቅራቢ ኩባንያ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የሚደግፉ መሳሪያዎች እንደተገጠሙላቸው ገልጿል። አልጋዎቹ ተገልጋዮች እንደየቁመትና ውፍረታቸው ሊያስተካክሏቸው የሚችሉ ናቸውም ብሏል። ሲተኙ ለስለስ ያለ ሙዚቃ መስማት የሚፈልጉ ካሉም መስማት ይችላሉ ነው የተባለው። በጃፓን ምግብ ቤቶች ተገጥመው አገልግሎት መስጠት የጀመሩት “ጂራፍናፕ” አልጋዎችን በሌሎች ሰዎች በሚበዙባቸው ስፍራዎች ለመግጠም መታቀዱም ተገልጿል። ሰዎች ቆመው የሚተኙበት “ጂራፍናፕ” አልጋ ስያሜውን ከረጅሟ ቀጭኔ ጋር አያይዞ አውጥቷል።

ጠቅላላ እውቀት

አፍሪካ ውስጥ ከ72 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ወጣቶች የመማር፣ ሥልጠና የማግኘትና የመቀጠር ዕድል እንዳላገኙ ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት አስታውቋል፡፡ ከእነዚህም መካከል አብዛኞቹ ወጣት ሴቶች መሆናቸውን ነው ያመለከተው። የዓለም ሥራ ድርጅት (አይኤልኦ) ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች በሚገኙት ሰባት አገሮች ማለትም ኢትዮጵያ፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ሴኔጋልና ዑጋንዳ ውስጥ ባካሄደው ጥናት አካሂዷል። በዚህም ጥናት ላይ እንደተመላከተው በአፍሪካ ከአራት ሰዎች መካከል አንዱ የመማር፣ የመሠልጠንና የመሥራት ዕድል ተነፍጓል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሁለት ሦስተኛው ወጣት ሴቶች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ. ከ2005 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን የቅጥር፣ የመማር ወይም ሥልጠና የማግኘት ዕድል አሽቆልቁሏል፡፡ ይህ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች በ2.8 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ በቀጣናው አንድ አራተኛ ወጣቶች አልተቀጠሩም ወይም ትምህርትም ሆነ ሥልጠና አላገኙም፡፡ በጥናቱ በተካተቱ ሰባት አገሮች ከ15 እስከ 29 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣት ሴቶች፣ በተመሳሳይ ዕድሜ ከሚገኙ ወንዶች ጋር ሲነፃፀሩ ከፍተኛ ያለመቀጠር፣ ያለመማርና ሥልጠና ያለማግኘት ሁኔታን አስመዝግበዋል፡፡ በኢትዮጵያ ወጣት ሴቶች ከወንድ እኩዮቻቸው ሲነፃፀሩ በሦስት እጥፍ ሥራ፣ ትምህርትና ሥልጠና አላገኙም፡፡ በናይጄሪያ፣ ሴኔጋልና ኡጋንዳ በሁለት እጥፍ ልዩነት ሲኖር፣ ባልተመጣጠነ መልኩ ሴቶች የቤት ውስጥ ሥራን ተሸክመው ይኖራሉ፡፡ ጥናቱ በተካሄደባቸው በሰባቱም አገሮች ከ25 እስከ 29 ዕድሜ ክልል በሚገኙ ወጣቶች፣ መሠረታዊ ትምህርት የተማሩት በከፍተኛ ደረጃ ከተማሩት ልቀው ተገኝተዋል፡፡ በአገሮቹ ወጣት ሴቶች ከወንዶች በትምህርት፣ በሥልጠናና በሥራ ዘርፍ ዝቅ ብለው ይገኛሉ፡፡ አገሮች በዘላቂ የልማት ግብ በተራ ቁጥር ስምንት ላይ ሥራን ለሁሉም ወጣቶች ተደራሽ ለማድረግ የተቀመጠውን አጀንዳ ለማሳካት፣ ፆታዊ አድልኦና መገለልን ከወዲሁ መዋጋትና ማስቀረት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁሟል፡፡

ይህን ያውቁ ኖሯል?

አንዲት ላም 3 ጥጃዎችን በአንድ ጊዜ ወለደች በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሸነን ኮሉ ወረዳ አንዲት ላም ሶስት ጥጃዎችን በአንድ ጊዜ መውለዷ ተሰምቷል፡፡ የላሟ ባለቤት ወይዘሮ አሻ አሊይ ላሚቱ ከዚህ ቀደም በአንድ ጊዜ ሁለት ጥጃዎችን ወልዳ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ አሁን ላይም በአንድ ጊዜ ሦስት ጥጃዎችን መውለዷን ነው ወይዘሮ አሻ ያረጋገጡት፡፡ የተወለዱት ጥጃዎች እና ላሚቷ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙም የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የጣሊያን የመከላከያ ስምምነቶችና የፖለቲካዊ ድጋፎች

በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣውን የጸጥታ ስጋት ተከትሎ፣ ጣሊያን ለባህረ...

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ”ንዋይ” የተሰኘ መተግበሪያን ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች...

የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ...

ሼክ ኢብራሂም ቱፋ በኢራን ኤምባሲ በመገኘት ሀዘናቸውን ገለጹ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼክ ኢብራሂም...