በህንድ እየተከናወነ ባለው 72ተኛው ‹‹ሚስ ወርልድ›› የቁንጅና ውድድር ላይ ኢትዮጵያን ወክላ የ19 አመቷ ሀሴት ደረጄ እየተወዳደረች ትገኛለች፡፡
ይህ ውድድር እንደሌሎች የቁንጅና ውድድሮች ሳይሆን የተለያዩ ፍልሚያዎችን ማለፍ የሚያስፈልግበት ነው፡፡
ቅዳሜና እሁድ የዚህ ውድድር አካል የሆነው የስፖርት ውድድር ተከናውኗል፡፡ ይህም ባድሜንተንንና ሩጫን ጨምሮ የተለያዩ ውድድሮችን ያካተተ ነው፡፡
በዚህ ውድድር ላይ የኢስቶኒያዋ ቆንጆ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘች ሲሆን ኢትዮጵያን የወከለችው ሀሴት ጥሩ ውጤት አምጥታለች፡፡
በሌላ በኩል ሀሴት በታለንት ውድድር ደግሞ ለሩብ ፍፃሜ ካለፉት 32ቱ መካከል ሆናለች፡፡ ውድድሩ ከ15 ቀናት በኋላ ሜይ 31 ይጠናቀቃል፡፡
