ኬንያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሰው ሰራሽ አስተውሎት አጠቃቀም አንደኛ ወጣች

Date:

አዲስ የወጣ ዓለም አቀፍ ሪፖርት እንዳመለከተው፣ ኬንያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አጠቃቀም ከዓለም አንደኛ ሆናለች። በሪፖርቱ መሠረት፣ በሀገሪቱ ካሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ውስጥ 97.5 በመቶ የሚሆኑት ባለፉት አንድ ወር ውስጥ ቢያንስ አንድ የAI ቴክኖሎጂ ተጠቅመዋል።

ይህ ቁጥር ከተጠኑት 54 ሀገራት ሁሉ ከፍተኛው በመሆኑ ኬንያን ቀዳሚ አድርጓታል፤ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በ94.2 በመቶ ሁለተኛ፣ ኢንዶኔዥያ ደግሞ በ93.6 በመቶ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ይህ ከፍተኛ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከሀገሪቱ የAI ዘርፍን በሕግ የማዋቀር ጥረት ጋር የተያያዘ ነው። በአንፃሩ እንደ አሜሪካ (71.5 በመቶ) እና ዩናይትድ ኪንግደም (62.8 በመቶ) ያሉ ታላላቅ ምዕራባውያን ሀገራት ከዚህ ውጤት በታች ይገኛሉ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በወር ውስጥ የAI ቴክኖሎጂን የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር 4.02 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፣ አብዛኛዎቹ ሰዎች AIን የሚጠቀሙት መረጃዎችን ለመፈለግ ነው።

capital fm kenya-

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...