ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

Date:

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢራን ከተሸነፈች በኋላ ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ።

አርብ ዕለት በኒውዮርክ ለደጋፊዎቻቸው ንግግር ያደረጉት ትራምፕ፣ አሜሪካ በቅርቡ ለዓለም የነዳጅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ እና የማዳበሪያ አቅርቦት ወሳኝ የሆነውን የሆርሙዝ የባሕር መስመር የግዛቷ አካል እንደምታደርግ ገልጸዋል።

“አሁን ላይ ከፍተኛ ሽንፈት እየገጠማት ያለችውን ኢራንን ድል አድርገን ከጨረስን በኋላ፣ በቅርቡ የሆርሙዝ ወሽመጥን የአሜሪካ ግዛት አድርጌ አውጃለሁ” ሲሉ ትራምፕ በኒው ዮርክ ግዛት፣ ጋርደን ሲቲ በሚገኝ የፖሊስ አካዳሚ በተደረገ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል። “ይህ እውነት ነው” ሲሉም አክለዋል።

ትራምፕ አርብ ዕለት ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ ምክንያት ስለጨመረው የነዳጅ ዋጋ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን አሜሪካውያን ተጨማሪ ክፍያ መክፈላቸውን መቀበል አለባቸው ብለዋል።

የፕሬዚዳንቱ ንግግር ከአምስት ወር በላይ በቆየው የኢራን ጦርነት ላይ ዋሺንግተን የፖሊሲ ለውጥ ስለማካሄዷ ወይም ታስቦበት የተሰነዘረ አስተያየት ስለመሆኑ ምንም የታወቀ ነገር የለም።

የኢራን ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካዜም ጋሪባባዲ የትራምፕን አስተያየት ከሰሙ በኋላ ወሽመጡ በኢራን ቁጥጥር እና ሥልጣን ሥር ይቆያል “ምንም አንረበሽም” በማለት ተናግረዋል።

አሜሪካ እና እስራኤል የካቲት 21፣ 2018 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ኢራን ላይ ጦርነት ካወጁ ወዲህ የሆርሙዝ ወሽመጥ በቋሚነት ተዘግቷል።

አሜሪካ እና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የኢራን ጦር በጀመረበት ወቅት የአገሪቱን የኒውክሌር ፕሮግራም ማስቆም ዋነኛ ዓላማቸው መሆኑን ሲናገሩ ነበር።

ኢራን በበኩሏ ለሚፈጸምባት ድብደባ በባሕረ ሰላጤው አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሠፈሮችን እንዲሁም በወሽመጡ በኩል የሚያልፉ ነዳጅ ጫኝ መርከቦችን በማጥቃት ምላሽ ሰጥታለች።

አሜሪካ ወደ ኢራን ወደቦች የሚገቡ እና የሚወጡ መርከቦችን እንቅስቃሴ የገደበች ሲሆን የሁለቱ አገራት መካረር የዓለም ነዳጅ ዋጋ ቅናሽ እንዳያሳይ አድርጎታል።

በሰኔ ወር አሜሪካ እና ኢራን ወታደራዊ እርምጃዎችን የሚያስቆም የመግባቢያ ሰነድ ቢፈራረሙም ከጥቂት ሳምንት በኋላ ፈርሶ ጦርነቱ ዳግም አገርሽቷል።

ትራምፕ አርብ ዕለት የአገሪቱ ሕግ አውጪዎች በተሰበሰቡበት ባደረጉት ንግግር፣ ኢራን ወደቦች ላይ የጣሉት እግድ ማንም ሊጥሰው የማይችል መሆኑን በመግለጽ አወድሰውታል።

እንዲሁም እርምጃውን በሆርሙዝ በኩል በሚደረግ የመርከቦች እንቅስቃሴ ላይ ለሚደገፉ አገራት የሚሰጥ የሕዝብ አገልግሎት አድርገው አቅርበውታል።

“እያደረግን ያለነው ነገር ለዓለም የሚሰጥ ታላቅ አገልግሎት መሆኑን ማስታወስ ብቻ ነው ፤ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ጭምር።” ሲሉ የተናገሩት ትራምፕ፣ “እግዱን ማስቆም እንደማይቻል” እና “የብረት ግንብ” ማለት እንደሆነ አስረድተዋል።

ትራምፕ በኒውዮርክ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በቅርቡ ለሚደረገው ምርጫ ለሪፐብሊካን ተመራጮች ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

የጆን ኤፍ ኬኔዲ መታሰቢያ ቤተ-መጻሕፍት ከአሜሪካ ኤምባሲ የ235 ሺህ ዶላር ድጋፍ ተደረገለት

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ውስጥ የሚገኘው የጆን...