ክፍያ በመቀበል የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን የሚያከራዩ በዝተዋል

Date:

የባንክ ሂሳብ ቁጥርን በመሸጥና በማከራየት የሚፈጸም የማጭበርበር ወንጀል መበራከቱን በፍትህ ሚኒስቴር፣ የጠቅላይ አቃቤ ህግ ዘርፍ ገለጸ።

አጭበርባሪዎች የሌሎችን ሰዎች የባንክ አካውንት (የሂሳብ ቁጥር) በመግዛት እና በመከራየት፣ በወንጀል የተገኘን ህገወጥ ገንዘብ ለማዘዋወር እየተጠቀሙበት እንደሆነ  በምርመራ ማረጋገጡን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ተናግሯል።

በፍትህ ሚኒስቴር፣ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ እጣወርቅ ተስፋዬ ” ወንጀለኞቹ አብዛኛውን ጊዜ የባንክ አካውንት የሚገዙት ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሰዎች ወይም ከቅርብ ጓደኞቻቸው ነው ” ብለዋል። ለዚህም የተወሰነ ገንዘብ እንደሚከፍሏቸው  አመልክተዋል።

አጭበርባሪዎቹ በሌላ ሰው ስም የተከፈተ አካውንት የሚፈልጉበት ዋና ምክንያት፣ ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለመደበቅ እና በወንጀል ያገኙትን ገንዘብ ያለ ስጋት እንደልብ ለማዘዋወር እንደሆነና ለዚህም ተግባራቸው በአብዛኛው የንግድ ባንክ አካውንቶችን እንደሚመርጡ ተናግረዋል።

ወንጀለኞቹ አካውንቱን እስከ 5,000 ብር በሚደርስ ክፍያ ከገዙ በኋላ፣ አዲስ ስልክ በመግዛት የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ (App) ያስጭናሉ። በመቀጠል የባንክ አካውንቱን ባለቤት የይለፍ ቃል ( #Password ) በመቀበል፣ ሙሉ የአካውንት የማስተላለፍና የመቆጣጠር ስልጣኑን በእጃቸው እንደሚያስገቡ አብራርተዋል።

” ከጓደኛዬ ወይም ከቤተሰቤ የመጣ ነው ፤ በአንተ አካውንት ገቢ ይደረግና እኔ ለምነግርህ ሰው አስተላልፍ፣ የተወሰነውን ደግሞ አንተ ያዘው ” በሚል ሰበብ በወንጀል የተገኘን ገንዘብ በሌላ ሰው አካውንት እንዲተላለፍ በማድረግ ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማሸሽ የሚፈልጉ አጭበርባሪዎች ቁጥር ስለመጨመሩ ተገልጿል።

ነገር ግን አንድ ሰው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የባንክ አካውንቱን ለሌላ አካል አሳልፎ ሰጥቶ፣ በአካውንቱ ላይ በወንጀል የተገኘ ህገወጥ ገንዘብ ከተዘዋወረና ይህ በምርመራ ከተረጋገጠ፣ በህግ ተጠያቂ የሚሆነው አካውንቱ በስሙ የተከፈተው ባለቤት እንደሆነ ተጠቁሟል።

” ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም ” ያሉት ም/ዳይሬክተሯ ” በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለአንድ የባንክ ሂሳብ ቁጥር ከ1,550 እስከ 5,000 ብር ክፍያ በመቀበል የሂሳብ ቁጥራቸውን አሳልፈው የሚሰጡ በዝተዋል ” ብለዋል።

በዚህ መንገድ ሰዎች እስከ 25 ዓመት በሚደርስ እስራት በሚያስቀጣ የወንጀል ድርጊት እየተሳተፉ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ እንደማያገኙ ተነገረ

በኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በበቂ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችል...

ገዳ ባንክ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፍኩ አለ

ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ113 በመቶ እድገት አሳይቷል ...

እስራኤል የኢራን ተደራዳሪዎችን ለመግደል እያሴረች እንደነበር ተዘገበ

አሜሪካና ኢራን ወሳኝ የሆነውን የተኩስ አቁም ስምምነት በደረሱበት እስራኤል...

ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው በፋብሪካ የተቀነባበረ  የበሬ ሥጋ ንግድ ተጀመረ

‘ራንቸርስ ፋይነስት’ የተባለው የኡጋንዳ የግል ሥጋ አቀናባሪ ኩባንያ፣ በየወሩ...