የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያ ገቡ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሶስት ቀናት ይፋዊ ጉብኝት ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፤ ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከተቀበሉ በኃላ ” ወደ ምድር ቀደምት ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ ” ብለዋል።

” ጉብኝትዎ በማሌዢያ እና ኢትዮጵያ መካከል እያደገ ያለውን ወዳጅነት እና ትብብር የሚያሳይ ሲሆን በሀገራችን የብልጽግና ጉዞ ውስጥም በጠቃሚ ጊዜ የተደረገ ጉብኝት ነው ” ሲሉ አክለዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከአመት በፊት በማሌዢያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገው እንደነበር ይታወሳል። በወቅቱም ከጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በወቅቱም በግብርና፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ታዳሽ ኃይል ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሁም ሌሎች ቁልፍ ሥራዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ለማጠናከር ስምምነት አድርገው ነበር።

በተጨማሪም የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የኢንቬስትመንት እድል እንዲጠቀሙ ፤ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበው ነበር።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...