▶️ ባለፉት ሶስት ወራት የተሰበሰበው የፌደራል መንግስት ገቢ 323 ቢሊየን ብር ደርሷል፤
▶️ ይህ አፈጻጸም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ112 በመቶ ጭማሪ ያለው ሲሆን ÷ በወቅቱ የተሰበሰበው ገቢ 152 ቢሊየን ብር ነበር፡፡
▶️ ባለፉት ሶስት ወራት ከወርቅ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፤
▶️ ከቡና ደግሞ 763 ሚሊየን ዶላር ተገኝቷል
▶️ ባለፉት 100 ቀናት ከአጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ 8.29 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ፤
▶️ ከወጪ ንግድ የሚመጣው የውጭ ምንዛሪ 57.6 በመቶ ደርሷል።
▶️ ባንኮች ባለፉት ሦስት ወራት እርስ በርሳቸው 19.2 ሚሊዮን ዶላር ሲያገበያይ፤ ብሔራዊ ባንክ ደግሞ 150 ሚሊዮን ዶላር አጫርቷል።
▶️ የሃዋላ ፍሰት 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፤
▶️ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ደግሞ 961 ሚሊየን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
▶️ አጠቃላይ ተቀማጭ ሃብት 3 ነጥብ 73 ትሪሊየን ብር ደርሷል ፤
▶️ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር የሥራ ስምሪት ለ671 ሺህ 589 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
▶️ በዚህ መሰረትም በሀገር ውስጥ ለ535 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል የተፈጠረ ሲሆን፤
▶️ ከዘርፍ አንጻርም
❇️ በግብርና ለ186 ሺህ ፣
❇️ በኢንዱስትሪ ለ122 ሺህ እንዲሁም
❇️ በአገልግሎት ለ227 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።
▶️ በተመሳሳይ በውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት ለ136 ሺህ 589 ዜጎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል፤
▶️ በተኪ ምርትም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል
▶️ ባለፉት ሦስት ወራት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በ13 በመቶ በማደግ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እድገቱን እየመራ ነው፤
▶️ በመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት በጠቅላላ 132 አዳዲስ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ወደ ሥራ ገብተዋል።
▶️ ለግሉ ዘርፍ እና ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች የሚደረገው የፋይናንስ ድጋፍ ከፍ ማለቱ በዘርፉ ላይ ትልቅ ለውጥ እያመጣ መሆኑን ተመላክቷል።
▶️ በሌላ በኩል ባለፉት ሶስት ወራት በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ሥራ መከናወኑ ተሰርቷል፤
▶️ በዘርፉ በአጠቃላይ 242 ሚሊየን ኩንታል ምርት የተሰበሰበ ሲሆን ፥ ከዚህ ውስጥ 74 ነጥብ 73 በመቶው የሰብል ምርት ነው ፤
▶️ 2.45 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ የሆርቲካልቸር ምርቶች እየለሙ ነው።
▶️ የሆርቲካልቸር ዘርፉ ልማት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር የ31.7 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፤
▶️ ባለፉት መቶ ቀናት 376 ሺህ 615 የውጭ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፤
▶️ 29 ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን ማዘጋጀት ተችሏል፤
▶️ በእነዚህ ኮንፈረንሶች ላይም 35 ሺህ 115 የውጭ ሀገር ዜጎች ተሳትፈዋል፤
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
