የትምህርት ማሻሻያ ያቀረቡ የሶስት እርከን ጭማሪ ተፈቀደ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በትምህርት ማሻሻያ የትይዩ ሽግግር ጥያቄ ያቀረቡ መምህራን በሚመለከት መመሪያ አስተላልፏል።

ደብዳቤዉ በአገር አቀፍ ደረጃ ከነባሩ የስራ ምዘና ስርዓት ወደ ነጥብ የስራ ምዘና በተደረገው የመምህራን ሽግግር መሰረት ከሐምሌ 01/2011 ጀምሮ፣ የከፍተኛ መምህር ሁለትና ሶስት ደረጃ በመታጠፉ ምክንያት የሶስት እርከን ጭማሪ እንዲያገኙ የተደረጉት መምህራን የትምህርት ማሻሻያ ሲያቀርቡ በትይዩ ወደ ሚቀጥለው ሳይክል ውስጥ ቢገቡም ምንም የደመወዝ ማስተካከያ አለመደረጉ ቅሬታ ማስነሳቱን ይገልጻል።

ቅሬታው የተነሳው የሥራ ክብደት ምዘና ሥራ ላይ ከመዋሉ ቀደም ብሎ የመምህራን ደረጃ እድገት መሰላል ዘጠኝ እንደነበር እና ከስራ ክብደት ምዘና በኋላ ግን ለመምህራን ተጠቃሚነት ሲባል ደረጃው ሰባት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የትምህርት ማሻሻያ እና ትይዩ የደረጃ እድገት ችግር በመምህራን ላይ በመፈጠሩ ነው።

ይህንንም ቅሬታ በማንሳት በኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በኩል ለቀረበው የማብራሪያ ጥያቄ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ነሐሴ 30/2017 ዓም ትምህርታቸውን ላሻሻሉ መምህራን የትይዩ ሽግግር አሰራርን በተመለከተ ያስተላለፈውን ሰርኩላር የክልልና የከተማ አስተዳደሮችም እንዲደርሳቸው መደረጉን ደብዳቤው ያትታል።

በተላለፈው ውሳኔ መሰረት እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ይህ ሰርኩላር የሚመለከታቸው መምህራን በሙሉ:-

1ኛ ይህ ሰርኩላር የሚመለከታቸው መምህራን በአገር አቀፍ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን መሰረት ከሐምሌ 1/2011 ጀምሮ በተደረገው ሽግግር ከጥር 2012 እስከ ጥር 2014/2017 ድረስ ቀጥታ ወደ ከፍተኛ መምህር ሁለትና ሶስት ደረጃ ለማደግ በሂደት ላይ እያሉ ሁለት ደረጃው የታጠፈባቸውና ወደ ጎን ሶስት እርከን ክፍያ ለተፈጸመላቸው እና ከዚህ ጥቅም በኋላ የትምህርት ማሻሻያ ላቀረቡት መምህራን ብቻ ይሆናል፡፡

2ኛ ከሐምሌ 1/2011 ጀምሮ በተደረገው ሽግግር ከጥር 2012 እስከ ጥር 2014 ድረስ የሶስት እርከን ጭማሪ ያገኙ መምህራን በ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን አሻሽለው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከተመደቡ በደረጃ 17 ከፍተኛ መሪ ላይ በመሆን ከመነሻው ወደ ጎን የሶስት እርከን ክፍያ ብር ከ15,340 ሳይበልጥ ከመስከረም 1 ቀን 2018 ጀምሮ እንዲፈጸምላቸው እንዲደረግ።

3ኛ ከሐምሌ 1/2011 ጀምሮ በተደረገው ሽግግር ከጥር 2012 እስከ ጥር 2014 ድረስ የሶስት እርከን ጭማሪ ያገኙ መምህራን ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት በማሻሻል የደረጃ ለውጥ ያመጡት የከፍተኛ መሪ መምህራን ወደ ደረጃ 16 በትይዩ ስለሚሻገሩ በመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ተመድበው ሲሰሩ ከመነሻው ወደ ጎን የሶስት እርከን ጭማሪ ሳያልፍ ከመስከረም 1 ቀን 2018 ጀምሮ ብር 13,998 እንዲፈቀድላቸው ተወስኗል።

ከላይ የተዘረዘሩትን የመምህራን የትምህርት ማሻሻያ ደመወዝ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች የስራ መደቦች ምዘና፣ ደረጃዎች ምደባና የደመወዝ ስኬል መሰረት እንዲፈጸም የተወሰነ ስለመሆኑ ቢሮው ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ ውሳኔው ለሚመለከታቸው መምህራን ብቻ በጥንቃቄ እየተረጋገጠ እንዲፈጸም ያሳሰበ ሲሆን ከተጠቀሰው ውጪ ለማይመለከታቸው ጥቅም መስጠት ተጠያቂነት እንደሚያስከትል ተገልጿል ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...