የነዳጅ ዋጋ መቀነስና የገበያ መረጋጋት

Date:

በመካከለኛው ምሥራቅ ባለው ውጥረት ምክንያት ሰማይ ደርሶ የነበረው የነዳጅ ዋጋ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱ “በቅርቡ ይጠናቀቃል” የሚል ተስፋ ሰጪ ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ ማክሰኞ ማለዳ ቅናሽ አሳይቷል።

በእስያ ገበያ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በ8.5 በመቶ ቀንሶ በበርሜል 92 ዶላር ሲሸጥ፣ የአሜሪካው ግብይት ደግሞ የ9 በመቶ ቅናሽ በማሳየት በ88.60 ዶላር ተመዝግቧል።

ምንም እንኳን ዋጋው አሁንም ከጦርነቱ መነሻ ጋር ሲነፃፀር የ30 በመቶ ብልጫ ቢኖረውም፣ በትራምፕ ንግግር የታየው የገበያ መረጋጋት በእስያ አክሲዮን ገበያ ላይ መነቃቃትን ፈጥሯል።

በተለይም አብዛኛው ነዳጅ ከቀጣናው የሚገቡት የእስያ አገራት፣ በኢራንና በአሜሪካ መካከል ያለው ወታደራዊ ግጭት ጋብ ማለቱ ለኢኮኖሚያዊ ትንሳኤያቸው ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ታምኖበታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...