የንግድ ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተጠየቁ

Date:

የንግድ ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች
ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ ተጠየቁ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ 23ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን «ስውር ትስስሮችን በማጋለጥ፤ የሙስና ወለድ ወንጀሎችን ሰንሰለት እንበጥስ!» በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ አከበረ።

በበዓሉ ንቅናቄ ላይ የተገኙት የቢሮው የሥነ-ምግባር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ከድጃ መሐመድ እንደገለጹት፤ ሙስናና ብልሹ አሠራር የሀገርን ልማት ከማደናቀፋቸውም በላይ የተቋማትን ተዓማኒነት የሚጎዱ ከባድ አደጋዎች በመሆናቸው ሁሉም ሠራተኛ ሀብቱን በማስመዝገብና ሕዝብን በታማኝነት በማገልገል የድርሻውን መወጣት አለበት።

በንቅናቄው ላይ የተሳተፉት የቢሮው ሠራተኞች በበኩላቸው፣ ለሙስና እድል የሚፈጥሩ ክፍተቶችን ለመዝጋትና ግልጽነትን ለማስፈን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ማሸጋገር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ለአገርና ለሕሊና ታማኝ በመሆን የሙስና ሰንሰለትን ለመበጠስ በሚደረገው ርብርብ የፊት መስመር ተላላፊ በመሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ አረጋግጠዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ አቻው ጋር ዛሬ ያደረገውን ወሳኝ ጨዋታ 1ለ0 ተሸነፈ !

በ2027 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ አራተኛ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

በአዲስ አበባ ለሶስት ቀናት የሚቆይ የንባብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

የንባብ ባህልን ለማነቃቃት ያለመ 15ኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ፌስቲቫል...

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ የኤንሪኮ ማቴይ ሽልማት ተሸለሙ

የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በአፍሪካና በአውሮፓ መካከል ያለውን...