የአሜሪካን ማዕቀብ ፑቲን ማጣጣላቸዉን ተከትሎ የኢኮኖሚ ህመሙ በቅርቡ ይሰማቸዋል ሲሉ ትራምፕ ዛቱ

Date:

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ በሩሲያ ሁለት ትላልቅ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን አጣጠጥለዋል፣ ይህንኑ ተከትሎ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እንደተናገሩት የሩሲያው ፕሬዝዳንት በቅርቡ የኢኮኖሚውን ህመም እንደሚሰማቸው ጠቁመዋል።

ትራምፕ በዋይት ሀውስ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት “እንዲህ አይነት ስሜት ስለሚሰማው ደስተኛ ነኝ” ብለዋል። “ይህ ጥሩ ነው ከስድስት ወር በኋላ ስለ ጉዳዩ አሳውቅዎታለሁ፤  ሁሉም ነገር እንዴት እንደሚሄድ እናያለን” ሲሉ ትራምፕ ተደምጠዋል፡፡

ፑቲን በትላንትናዉ እለት በግዙፎቹ የሩሲያ የነዳጅ ኩባንያዎች በሆኑት በሮስኔፍት እና ሉኮይል ላይ የተጣለውን ማዕቀብ “ወዳጅነት የጎደለው ድርጊት” ሲሉ ገልጸው ነገር ግን ድርጊቱ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን ጉዳት አቅልለውታል።”በተፈጥሯቸው ማዕቀቦች ከባድ ናቸው እናም የተወሰነ ውጤት ይኖራቸዋል፤ ነገር ግን በኢኮኖሚያችን ጤና ላይ ምንም አይነት ተጽእኖ አይኖራቸውም” ሲሉ ፑቲን ተደምጠዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ማዕቀቡን ረቡዕ እለት የጣለችው ሞስኮ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማቆም የሰላም ሂደት ላይ “ከባድ ቁርጠኝነት ስለሌላት ነው” ማለቷ ይታወሳል፡፡

የግምጃ ቤት ዲፓርትመንት በመግለጫው እንዳስታወቀው እርምጃዎቹ የሩስያን የኢነርጂ ዘርፍ “የክሬምሊን ለጦር መሣሪያዎቿ ገቢ የማሳደግ አቅምን ለመጨመር” እና “የተዳከመ ኢኮኖሚዋን ለመደገፍ” ያነጣጠረዉን እንቅስቃሴ ይጎዳል ብሏል።የግምጃ ቤት ፀሐፊ ስኮት ቤሴንት በመግለጫቸው ላይ “ግድያውን ለማስቆም እና የተኩስ ማቆም እንዲደረስ ጊዜው አሁን ነው” ብለዋል።

#ዳጉ_ጆርናል

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...