Home ቴክኖ-ቢዝ የአየር ብክለትን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

የአየር ብክለትን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

የአየር ብክለትን እንዴት መቀነስ ይቻላል?

መንግስት

የአየር ብክለት የቀነሱ ሀገሮችን ተሞክሮ ወደ ሀገራችን በማምጣት ተግባራዊ ማድረግ፡፡

       – ሕግ እና ደንቦችን በማውጣት ማህበረሰቡ እንዲተገብር ማረግ፡፡

       – ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን በመቅረፅ ለህብረተሰቡ ማሳወቅ፡፡

       – በሀገራችን እንደ ባህል እየተቆጠረ የመጣውን ችግኝ ተከላ ማስቀጠል፡፡  

       – በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪና እና ሞተር ሳይክሎችን አምራቹንም ሆነ የሚያስገቡትን  ባለሀብቶች መደገፍ፡፡

ኢንዱስትሪዎች

በጭስም ሆነ በፈሳሽ መልክ የሚለቁትን በካይ ነገር መቀነስ፡፡

– ቴክኖሎጂካል ኢኖቬሽንን ጥቅም ለይ በማዋል የሚለቁትን በካይ ነገር ወደ ሌላ  ጥቅም ሰጪ  ሀይል መቀየር

– ፊታቸውን ወደ ታዳሽ ሀይል በማዞር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እና የበካይ ጋዝ ልቀት  የሌላቸው ፋብሪካዎችን መገንባት፡፡

ግለሰቦች

የእለት ተዕለት እንቅስቃሴያችንን በተቻለን አቅም ከነዳጅ ጥገኝነት መለየት

            – ሳይክሎችን መጠቀም

            – በእግር መጓዝ

            – አካባቢን ሊበክሉ ሚችሉ ነገሮችን በህብረት ማስወገድ

            – የግድ ካልሆነ በስተቀር የግል መኪናችንን አቁመን በህዝብ ትራንስፖርት በጓጓዝ፡፡

            – ከመንግስት የሚያወጣቸውን ህግ እና ደንቦችን ተግባራ ማረግ፡፡

            – በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪና እና ሞተር ሳይክሎችን መግዛት፡፡

በአለማችን በብዛት የኤሌክትሪክ መኪና እና ሞተር ሳይክሎችን የሚጠቀሙ ሀገሮች

1. ኖርዌይ

2. ጃፓን

3. ደቡብ ኮሪያ

4. ቻይና

5. ፈረንሳይ

ኖርዌይ ከ1000 የቤት መኪኖቿ ውስጥ 30.2% በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች ናቸው፡፡ በ2018 በተደረገ ጥናት ጃፓን ውስጥ 7.5 ሚሊዮን በኤሌክትክ የሚሰሩ መኪኖች ነበሩ፡፡ ደቡብ ኮሪያ በ110.714 ኪ.ሜ የመንገድ ርዝመት ላይ 3910 የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጅ የሚያረጉበት charge station አለ ይህ ማለት በየ 28.3 ኪ.ሜ ርቀት ላይ አንድ charge station አለ ማለት ነው፡፡

  • በአለም ላይ በኤሌክትሪክ ቻርጅ ከሚሰሩ ካምፓኒዎች ጋር ብዙ ሼር ያላት ሀገር አንደኛዋ ቻይና ናት <<EV CARD>>ከ 110.000 በላይ ፈጣን ቻርጅ ማረጊያ ስቴሽን በየመንገዱ ላይ በመትከል የአለምን ሪከርድ ሰብራለች ይህ ማለት በየ 43.5ኪ.ሜ ርቀት ላይ አንድ የ charge station አለ ማለት ነው፡፡

ያደጉ ሀገሮች እነ ኖርዌይ ከ2025 ማትም ከ 4 አመታ በኃላ በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ከሀገራቸው ሙሉ ለሙሉ ሊያስወጡ እቅድ ይዘዋል

            እኛስ እንደ መንግስት እና እንደ ግለሰብ ምን አስበናል?

  • መንግስት ቀረጥ በመቀነስ በዚህ ሀገርን በማዳን ላይ የተሰማሩትን ግለሰቦች ማገዝ አለበት፡፡
  • በቻርጅ የሚሰሩ ተሸከርካሪ የገዙትን ሰዎች በመሸለም ፣በተለያየ ቦታዎች ላይ ቅድሚያ በመስጠት ለምሳሌ ያህል ነጻ ፓርኪንግ እና የመሳሰሉትን በማረገግ ማበረታታት ይህ ሁኔታ ሌላውንም ያነሳሳል፡፡
  • አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ካደጉ ሀገሮች ጋር እኩል መራመድ ባንችል እንኳን እግር በእግር እየተከተልን የቴክኖሎጂ ተቋዳሽ መሆን አለብን እነ ኖርዌይ በ2025 ሙሉ በሙሉ ከነዳጅ ነፃ የሆኑ መኪኖችን ለመጠቀም አስበዋል፡፡

በቅርቡ 8/16/2021 አለማችን ላይ ያሉ ግዙፍ መኪና አምራች ካምፓኒዎች በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ከፋብሪካቸው አስወግደው በኤሌክትክ ወደሚሰሩ መኪኖች ይቀይሯቸዋል የዛኔ ከመሯሯጥ መንግስት ወይም ባለሀብቶች ካሁኑ ለምን ቻርጅ ስቴሽን አይገነቡም፡፡ ይህ ለመንግስትም ሆነ ለባለሀብቱ የማስታውሰው ማሳሰቢያ ነው፡፡          

ከተለያየ የዜና አውታሮች እና የመረጃ መረቦች የተገኙ ቅንጭብጭብ መረጃዎች

AQI ቢለካም ባይለካም ሁኔታዎች ወደ ተባባሰ ችግር እያመሩ እንደሆነ የስሜት ህዋሳቶቻችን ይነግሩናል እያመለከቱንም ይገኛሉ፡፡ ተ/ሀይማኖት፣ ቦሌ፣ ቃሊቲ፣ ሜክሲኮ፣ መርካቶ AQI ሲለካ WHO ጎጂ ነው ብሎ ካስቀመጠው የአየር ጥራት በ8 እጥፍ በልጦ እንደተገኘ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡  መኪኖች 100% ነዳጁን የሚያቃጥሉ ከሆነ ምንም አይነት ጭስ አይወጣም ነገር ግን ምን ያህሉ ሀገራችን ውስጥ ያሉት መኪኖች መቶ በመቶ ነዳጁን ያቃጥላሉ??

አንድ አንድ ሀገሮች ከመኪና ሞተር የሚወጣው ጭስ ወደ አየር ሳይቀላቀል የጭስ ማውጫ ጫፉ ላይ catalytic converter የተባለ መሳሪያ በመግጠም ተብላልቶ ተቃጥሎ ያላለቀውን ሰልፈር convert እንዲሆን መኪናቸው ጭሥ ማውጫ ላያ በመግጠም ለችግሩ መፍትሄ ወሥደዋል፡፡ ሰልፈሩ ኮንቨርት ከሆነ ካርበኑም አብሮ ስለሚነድ ወደ ጋዝነት ይቀየራል ችግሩን መቶ በመቶ ባይቀርፈውም ቢያንስ PM  ይቀንሳል፡፡  አስመጪዎች ይህን መሳሪያ በማስገባት ሀገራቹን ታደጉ እያልኩ ጥሪዮን አቀርባለሁ፡፡ አንዱ የኛ ሀገር የሚነሳው ችግር የ fuel quality/ የነዳጅ ጥራት ችግር ነው ብዙ Sulfur content ያለው ነዳጅ ሥለምንጠቀም፡፡ µg/M3 microgram per meter squire ይህ ማለት በአንድ ሜትር ኩብ አየር ውስጥ ምን ያህል suspended particle አለ ማለት ነው ፓርቲክሎቹ አቧራ ሰልፈር pm ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የመንገድ አካፋይ ብረቶችን ፖሎችን አሊያም ማንኛውም መንገድ ላይ ያሉ ነገሮችን ብናይ በጣም ጠቁረው እናያን ያጥላሸት ከየት የመጣ ነው ብለን ጠይቀን እናውቃለን፡፡ ከፍተኛ የመሬት አቀማመጥ ያላቸው ቦታዎች ላይ የአየር ብክለት ወደ ዝቅተኛ ቦታ ይሄዳል፡፡ የመጀመሪያ ተጎጂው ነጂው ነው ሲነዳ የሚውለው በመቀጠል እዛ አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ከዛ ሁሉም የሰው ዘር፡፡ በየአመቱ በአየር ጥራት መጉደል ምክኒያት 9000 ሰው እንደሚሞት የለንደን ከተማ ከንቲባ ለተለያዩ የዜና አውታሮች አሳውቀዋል ይህን ለማካካስ ከንቲባው ወደ ለንደን የሚገቡ ቤንዚል እና ናፍጣ የሚጠቀሙ ከ2006 በኃላ የተመረቱ መኪኖች ወደ ለንደን ሲገቡ 10 ፓውንድ እንዲከፍሉ በማረግ በሚገባው ገቢ አየር ንብረቱን ለመደጎም ተሞክሯል፡፡

-የተበከለ አየር በውስጡ የሚይዛቸው ኬሚካሎች የሰው ቆዳ ካለግዜው ያረጀ እንዲመስል ያረጋል የዘርፉ ተመራማሪ የሆነው አልስተን አችሰን የተባለ አሜሪካዊ  ከ30 -40 የዕድሜ ክልል ላይ ያሉ 200  የከተማ እና የገጠር ሴቶች ላይ ጥናት አርጎ ሌላ ሰዎችን ሲያስገምት ገማቹ በገጠር የሚኖሩትን አስከ 10 አመት እየጨመረ ገምቷል አልስተን በጥናቱ ማጠቃለያ ላይም የተበከለ አየር የመተንፈሻ አካላትን ብቻ ሳይሆን የሚጎዳው በቆዳችን ላይም አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳለው አመላክቷል፡፡

የከተማው ነዋሪ እየሰሳበ ያለውን አየር ምን ያህል ያውቀዋል?

– ከ60-65 በመቶ መኪኖች እዚሁ አዲስ አበባ ይገኛሉ

– ሀገራችን ኢትዮጲያ መኪና በዝቶ ሳይሆን የምንጠቀመው ነዳጅ ውስጥ ያለው የ ሰልፈር መጠን ከሌላ ሀገሮች አንጻር ብዙ ነው፡፡ የpetroleum ጥራት ላይ መሰራት አለበት፡፡

– በየዓመቱ ቦሎ ምርመራ ይካሄዳል በዚህ ግዜ አብሮ ምርመራ ቢደረግ፡፡

– import issue ጉምሩክ አካባቢ ያገለገሉ መኪኖች እዲገቡ ባለሀብቱን የሚያበረታታ አሰራር ተዘርግቷል ያን ማስተካከል አዲስ የሚስገቡትን ታክሱን በመቀነስ ማበረታታት፡፡

– ለምሳሌ የጀርመኗ ፍራይቡርግ ከተማን ብንወስድ 500 ኪ.ሜ የሚደርስ የሳይክል መንገድ አላት እዚ አዲስ አበባ ወደ ጀሞ አካባቢ ለሳይክል ተብሎ የተሰራ መንገድ አስተውየለው በቂ አደለም አሁንም ሊሰራበት ይገባል፡፡

– 17% የሚሆነው የለንደን ነዋሪ ለከባድ እና መካከነኛ ጉዳት ለሚዳርግ ጎርፍ የተጋለጡ ናቸው ይህ ማለት ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ የለንደን ነዋሪዎችበዚህ ስጋት ውስጣ ናቸው፡፡የከተማው አስተዳደር የጎርፍ ስጋትን ለመከላከል የተለያዩ መላዎችን በመዘየድ የህብረተሰቡን ደህነት ለማረጋገጥ እየሰራ ነው፡፡ የአየር ለውጡ ባስከተለው የጎርፍ አደጋዎች ምክኒያት በተያዘው የፈረንጆች 2021 ብቻ ብዙ ሀገራት ላይ መንገዶች እንዳልሆኑ ሆነዋል፣ ድልድዮች ፈርሰዋ፣ ብዙዎች የት እንደገቡ ሳይታወቅ ጠፍተው ቀርተዋል፣ የብዙ ሰው ነፍስ ጠፍቷል፣ የብዙ ሰው ንብረት ወድሟል፣ ሆስፒታሎች፣ት/ቤቶች፣ ብዙ የህዝብ መገልገያዎች ወድመዋል፣ ብዙ ውድ ተሸከርካሪዎች ተንሳፈው ሩቅ ሄደው አይሆኑ ሆነዋል፣ ብዙ ገንዘብ የፈሰሰባቸው ውድ ቤቶች ወድመዋል ፈራርሰዋል፡፡