የአየር ንብረት ለውጥ ለ 4 ቢሊየን የዓለም ህዝብ ተጨማሪ የአንድ ወር ከፍተኛ ሙቀት እንደሚያስከትል ተነገረ

Date:

ከአለም ህዝብ ግማሽ ያህሉ በሰዉ ሰራሽ ምክንያት የአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ ባለፈው አመት ተጨማሪ አንድ ወር ከፍተኛ ሙቀት አጋጥሟቸዋል ሲል አዲስ ጥናት አመልክቷል።

ከፍተኛ ሙቀት ለሞት እና ለበሽታዎች መንስኤ ሆኗል::

የግብርና ሰብሎች እና የኃይል እንዲሁም የጤና አጠባበቅ ስርዓቶች ላይ ጫና ፈጥሯል::

ሪፖርቱን ከዓለም የአየር ሁኔታ መግለጫ፣ ክላይሜት ሴንትራል የተሰኘ ተቋም እና ቀይ መስቀል ጋር በመሆን ይፋ ተደርጓል፡፡

ተመራማሪዎች ከ1991 እስከ 2020 ባለው ጊዜ ውስጥ በተወሰነ ቦታ ከተመዘገበው የሙቀት መጠን ከ90 በመቶ በላይ ሙቀት ተብሎ የተገለፀውን የከፍተኛ ሙቀት አደጋዎችን ለመለየት ከግንቦት 1 ቀን 2024 እስከ ሜይ 1 ቀን 2025 ያለውን የአየር ሁኔታ መረጃ ተንትነዋል።

ወደ አራት ቢሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ወይም 49 በመቶው የዓለም ሕዝብ ቢያንስ ለ 30 ቀናት ከፍተኛ ሙቀት አጋጥሟቸዋል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በወቅቱ 67 ከባድ የሙቀት ክስተቶች ተገኝተዋል፡፡

“ምንም እንኳን ጎርፍ እና አውሎ ነፋሶች ብዙ ጊዜ በዜናዎች ላይ የበላይነት ቢኖራቸውም ሙቀት በጣም ገዳይ የሆነ ክስተት ነው” ሲል ዘገባው ገልጿል።

እንደ ባለሙያዎች ትንታኔ ከሆነ ከከፍተኛ ሙቀት ጋር የተቆራኙት ሞት ብዙም ያልተዘገበ ወይም የተሳሳተ ስያሜ የተሰጣቸው ናቸው።

በለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ የአየር ንብረት ሳይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና ከሪፖርቱ አጥኚዎች መካከል አንዱ የሆኑት ፍሬደሪክ ኦቶ እንዳሉት የሙቀት ሞገዶች ዝምተኛዉ ገዳይ ናቸው ብለዋል።

“ሰዎች በጎዳና ላይ በሙቀት ማዕበል ውስጥ አይሞቱ፤ ሰዎች በሆስፒታል ውስጥ ወይም በደንብ ባልተሸፈነ ቤት ውስጥ ይሞታሉ እና ስለዚህ አይታዩም” ብለዋል ።

አክለውም “በእያንዳንዱ በርሜል ዘይት በተቃጠለ ቁጥር እና እያንዳንዱ ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ሲለቀቅ እንዲሁም በእያንዳንዱ የሙቀት መጠን መጨመር የሙቀት ሞገድ ብዙ ሰዎችን ይጎዳል ሲሉ ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...

በፌደራሉ ሠራዊት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት መቀስቀሱ ተገለጸ

ከሱዳን ጋር በሚዋሰነው የሰሜናዊ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ በሚገኝ...

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...