የአዲስ አበባ የ2019 በጀት 502.27 ቢ. ብር ሆኖ ፀደቀ

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል 502 ነጥብ 27 ቢሊየን ብር አጠቃላይ በጀት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ይህ የዘንድሮው በጀት ከባለፈው ዓመት (2018 ዓ.ም) ጋር ሲነጻጸር የ152 ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር (የ43.5%) እጅግ ከፍተኛ ብልጫ አሳይቷል።

ከተመደበው አጠቃላይ በጀት ውስጥ አንበሳውን ድርሻ የያዘው 359 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለካፒታል ወጪዎች የተመደበ ሲሆን፣ 142 ነጥብ 97 ቢሊየን ብር ለመደበኛ ወጪ እንዲሁም 16 ቢሊየን ብር ለመጠባበቂያ በጀት እንዲሆን ተወስኗል።

ይህ ግዙፍ በጀት በዋናነት የከተማዋን የልማት ስትራቴጂዎች ለማሳካትና የኢኮኖሚ ማረጋጋት ሥራዎችን በመሥራት የኑሮ ውድነትን ለማቃለል ያለመ ነው።

በተጨማሪም ለአዳዲስ የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለኮሪደር ልማትና ለተጀመሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ማጠናቀቂያ፣ ለትራንስፖርትና ትራፊክ ፍሰት ማሻሻያ፣ ለቤት ልማት፣ ለውሃ አቅርቦት እና ለመንገድ መሠረተ-ልማት ማስፋፊያ የሚውል ሲሆን፤ የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ብልሹ አሠራርንና ሌብነትን ለመዋጋት በትኩረት እንደሚሠራበት ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...