የኢራን መርከቦች የአሜሪካን እገዳ ለመስበር አዳዲስ ስልቶችን እየተጠቀሙ ነው

Date:

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችውን የባሕር ላይ እገዳ ተከትሎ፣ ከቴህራን ጋር ግንኙነት ያላቸው መርከቦች በሆርሙዝ የባሕር መስመር ላይ ክትትልን የሚያሳስቱ የቴክኖሎጂ ስልቶችን በስፋት እየተጠቀሙ መሆኑን ኒውዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

መርከቦቹ መገኛቸውን የሚያሳውቁ መሣሪያዎችን በማጥፋት ራሳቸውን ከራዳር ይሰውራሉ፤ አልያም ደግሞ የተሳሳተ መረጃ በመላክ ሌላ መርከብ መስለው ለመታየት ይሞክራሉ።

የባሕር ላይ ደህንነት ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ፣ መርከቦቹ የክትትል ቀጠናውን ለማለፍ የሐሰት መታወቂያዎችን በመጠቀም አሜሪካ የጣለችውን ጥብቅ ቁጥጥር እየተፈታተኑት ይገኛሉ።

ይህ አይነቱ የማታለል ስልት ቀደም ሲል በሩሲያ መርከቦች ላይ ይስተዋል የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን በሆርሙዝ የባሕር መስመር ላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱ ታውቋል።

ይህም የንግድ መርከቦችን እንቅስቃሴ በትክክል ለመከታተል አስቸጋሪ ከማድረጉም ባለፈ፣ በዓለም አቀፍ የውኃ መስመር ላይ ከፍተኛ አለመረጋጋትና እርግጠኛ አለመሆንን እየፈጠረ ነው።

መርከቦቹ እንዲህ ያለውን አደገኛ የ”ድብብቆሽ” ጨዋታ የሚጫወቱት የአሜሪካን ወታደራዊ እገዳ ጥሰው የነዳጅና የምግብ ምርቶችን ለማጓጓዝ መሆኑን የባሕር ላይ መረጃ ተንታኞች ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...