ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲተያይ የ47.57 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ በሰጡት በዚህ መግለጫ፣ ባንኩ በበጀት ዓመቱ በዋና ዋና የስኬት መለኪያዎች ባንኩ ከፍተኛ ስኬት አስመዝግቧል ብለዋል።
ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በተለያዩ ዘርፎች 648 ቢሊየን ብር ብድር ሰጥቷል ሲሉ ፕሬዘዳንቱ አስረድተዋል።
ከ6 ዓመታት በፊት ባንኩ ይሰጥ ከነበረው ብድር 90 በመቶው ለመንግሥት ተቋማት የሚውል እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ ዘንድሮ ግን ይህ አካሄድ ተቀይሮ 90 በመቶው (588 ቢሊየን ብር) ለግል ዘርፉ መሰጠቱን አስረድተዋል ።
በአጠቃላይ የተሰጠው ብድርም 1.64 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ከሪፖርቱ ላይ ተመልክተናል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዓመቱ ውስጥ ከ707.4 ቢሊየን ብር በላይ አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰቡን፣አጠቃላይ ተቀማጩ 2.4 ትሪሊዮን ብር መድረሱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።
ባንኩ በበጀት አመቱ ከወጪ ንግድ 2.1 ቢሊየን ዶላር አግኝቻለሁ ያለ ሲሆን፣ ባባለፉት ሁለት ዓመታት ያገኘው አጠቃላይ የውጭ ምንዛሪ መጠን 5.6 ቢሊየን ዶላር ደርሷል ተብሏል።
ባንኩ በቀጣዩ በጀት ዓመት 832 ቢሊየን ብር አዲስ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ፣አጠቃላይ ገቢውን ደግሞ 360 ቢሊየን ብር ለማድረስ እቅድ እንዳለው ተናግሯል።
