የኢንጂነር ታደለ ብጡል የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈጸመ

Date:

ኢንጂነር ታደለ ብጡል የባንክ ባለሙያ፣ ሲቪል መሀንዲስ እና ደራሲ ሲኾኑ፣ ማራዥት እና ሦስትዮሽ የተሰኙ የግጥም መድብሎች እንዲሁም የክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል፣ የሀኪም ወርቅነህ እሸቴ፣ የአፄ ቴዎድሮስ እና የልዑል አለማሁ ቴዎድሮስን ግለ ታሪኮች ፅፈዋል። የአማርኛ የምልክት ቋንቋ መዝገበ ቃላትንም አዘጋጅተዋል። ደራሲ እና ኢንጂነር ታደለ ብጡል በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ላይ በመሳተፍም ይታወቃሉ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የማታ ትምህርት ያስጀመሩ ናቸው። በታዋቂው አርበኛ የተሰየመውን ወንዲራድ ት/ቤትን ከሌሎች ጋር በመሆን አቋቁመዋል። የአክሱም ሀውልት ብሄራዊ አስመላሽ ኮሚቴ አባልም ነበሩ። የተለያዩ ባህላዊ እና ትውፊታዊ ቅርሶችን ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት በራሳቸው ወጪ ገዝተው በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተለያዩ ሙዚየሞች በመለገስ ታሪካዊ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የ2008 ዓ.ም የበጎ ሰው ተሸላሚው የሀገር ባለውለታ ኢንጅነር ታደለ ብጡል በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በ97 ዓመታቸው ነሐሴ 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉ ሲኾን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም፣ ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...