የወንጀል ጥግ

Date:

ኢየሱስ ነኝ በሚል 300 ሺህ ዩሮ የተቀበለው አጭበርባሪ ተያዘ፡-

ግለሰቡ አዛውንቷን በገነት ውስጥ ለምታሳልፊው ህይወት ወጪ ይሆንሻል በሚል ገንዘቡን እሱ ጋር እንድታስቀምጥ አድርጓል ተብሏል፤ እየሱስ ነኝ በሚል 300 ሺህ ዩሮ የተቀበለው አጭበርባሪ ተያዘ። በሀገረ ስፔን እኔ እየሱስ ነኝ በሚል አንድ አዛውንትን በማጭበርበር ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተቀበለ ተገልጿል። ግለሰቡ አዛውንቷን በገነት ህይወትሽ ለሚያስፈልጉሽ አንዳንድ ነገሮች በከፍተኛ ወለድ ያላትን ገንዘብ እሱ ባዘጋጀው አነስተኛ እቃ ውስጥ እንድትቆጥብ እድርጋል ተብሏል። እስፔራንዛ የተሳኙት እኝህ አዛውንትም ከእየሱስ እንደተደወለላት፣ ገነት እንደምትገባ እና ገንዘቧን እንድትቆጥብ እንደተነገራት ለቤተሰቦቿ መናገራም ተገልጿል። አዛውንቷ ሴትዮም እራሱን እየሱስ ነኝ በሚለው ግለሰብ በመታለል ላለፉት ስድስት ዓመታት ያላትን ገንዘብ ሁሉ እያወጣች ሰጥታለች ተብሏል። ግለሰቧ ከፈረንጆቹ 2013 ጀምሮ እየሱስ ነኝ ብሎ ለነገራቸው ግለሰብ ገንዘባን ስትሰጥ ቆይታለች ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግባል። አዛውንቷ ከእሷ በተጨማሪም ለሴት ልጇም ቅዱስ እንደሆነች ስትነግራት ቆይታለች የተባለ ሲሆን ልጅቷ ግን እንደ እናቷ አለመታለሏ ተገልጿል። በገነት ውስጥ የተንደላቀቀ ህይወት ለማሳለፍ ቁጠባ ጀምሬያለሁ ያለችው ይህች ግለሰብም በሁለት ባንኮች ውስጥ የነበራትን ገንዘብ ሳይቀር እያወጣች እየሱስ ነኝ የሚለው ሰው ባዘጋጀላት ማጠራቀሚያ እቃ ውስጥ ስታስቀምጥ እንደቆየችም ገልጻለች። እራሱን እየሱስ ነኝ በሚል ማጭበርበሩ የተደረሰበት ግለሰብም ወንጀል እንዳልፈጸመ ቢከራከርም የሀገሪቱ መርማሪ ባደረጋቸው የስልክ እና ሌላሎች ምርመራዎች ጥፋተኛ ኮኖ ተገኝቷል ተብሏል። የስፔን ፍርድ ቤት ግለሰቡ የአዛውንቷን በእድሜ መግፋት እና የማሰላሰል አቅምን በመጠቀም በማጭበትበር ወንጀል የስምንት ዓመት እስር ተላልፎበታል።

ድንቃይ

60 አመታት እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም የሚሉት 80 አመት አዛውንት

ቬትናማዊው ታይ ንጎክ በ20 አመታቸው ከገጠማቸው ከባድ ህመም በኋላ ከእንቅልፍ ጋር መለያየታቸውን ይናገራሉ፡፡ የህክምና ባለሙያዎች ግን አዛውንቱ ምናልባት ስለማይሰማቸው እንጂ በቀን ውስጥ የተወሰኑ ስአታት መተኛታቸው አይቀርም ባይ ናቸው፡፡ የሰው ልጅ አይደለም ለዓመታት ለጥቂት ቀናት የእንቅልፍ መዛባት ከገጠመው በጤናው ላይ ምን ይዞ እንደሚመጣ መገመት አይከብድም። ከወደ ቬትናም የተሰማው ዜና ግን ለአመታት መነጋገሪያ ሆኖ ዘልቋል። በዚህ አመት 80ኛ አመታቸውን የያዙት ታይ ንጎክ፥ ላለፉት ስድስት አስርት አመታት እንቅልፍ ይዞኝ አያውቅም ይላሉ። ቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው እና ጎረቤቶቻቸውም ጭምር ንጎክ ተኝተው አይተዋቸው እንደማያውቁ ነው የሚገልጹት። አዛውንቱ በፈረንጆቹ 1962 (የ20 አመት ወጣት እያሉ) ከገጠማቸው ህመም ወዲህ ከእንቅልፍ ጋር ተሰነባብተዋል። ንጎክ በዘመናዊውም ሆነ ባህላዊ ህክምና ያልሞከሩት ነገር የለም፤ ከዛሬ ነገ ይሻሻላል ብለው የጠበቁት ጉዳይም ቀናት ቀናትን እየወለዱ ሲሄዱ እየተላመዱት መምጣታቸውን ይናገራሉ።  “የእንቅልፍ ማጣት ችግሩ በጤናዬ ላይ ያስከተለው ተጽዕኖ ስለመኖሩ እንጃ፤ እኔ እስካሁን ምንም ችግር አልገጠመኝም፤ ጤነኛ ነኝ፤ እንደማንኛውም አርሶ አደር ስራዬን እከውናለው” ብለዋል የ80 አመቱ አዛውንት ታህን ኔይን ከተሰኘው የቬትናም ድረገጽ ጋር ባደረጉት ቆይታ። ድሪው ቢንስኪ የተባለ ዩትዩበርም በቅርቡ በእኝህ አዛውንት ቤት ካሜራውን ደቅኖ የተባለውን ለማረጋገጥ ሞክሯል። ከአሜሪካ አሪዞና ወደ ገጠራማዋ የንጎክ መንደር የተጓዘው ድሪው “ከአመታት በፊት ዜናውን እንደተመለከትኩ ሊሆን አይችልም ነበር ያልኩት፤ በወቅቱ የአዛውንቱ መኖሪያ አካባቢ ስላልተገለጸም በአካል ሄጄ ለማረጋገጥ አልቻልኩም፤ አሁን ግን ከንጎክ ጋር ሌሊቱን ሙሉ ቁጭ ብዬ አድሬ እውነትነቱን በካሜራዬ ይዣለሁ” ይላል። አሜሪካ በቬትናም ባካሄደችው ጦርነት (ከ1955 እስከ 1975) ምክንያት በእጃቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ንጎክ ምናልባትም በጦርነቱ የተመለከቷቸው ዘግናኝ ነገሮች እንቅልፍ እንዲያጡ ምክንያት ሳይሆኑ እንዳልቀረም ነው ድሪው የሚገልጸው። የህክምና ባለሙያዎች ግን አዛውንቱ ምናልባትም ተኝተው እንቅልፍ የመያዝ ስሜት አልተሰማቸው ይሆናል እንጂ ሳይተኙ ለ60 አመታት መዝለቅ አይችሉም ይላሉ። በአውስትራሊያ የእንቅልፍ እና ተያያዥ ጉዳዮች ሀኪም የሆኑት ዶክተር ቪካስ ዋድህዋ፥ አንዳንድ የእንቅልፍ መዛባት ችግሮች እንቅልፍ የመያዝ እና የመንቃት ስሜትን ለመለየት ያስቸግራሉ ብለዋል። በመሆኑም የ80 አመቱ አዛውንት በቀን ውስጥ ለምን ያህል ስአት ወይም ደቂቃ እንደሚያርፉ ለማረጋገጥ ባይቻልም ቢያንስ አጭር ሸለብታ ይይዛቸዋል ነው የሚሉት። ታይ ንጎክ በርግጥም ላለፉት ስድስት አስርት አመታት ከእንቅልፍ ከተለያዩ በምድራችን ረጅሙን እድሜ የኖሩ አዛውንት ይሆናሉ።

ጠቅላላ እውቀት አየርላንድ ወደ ደሴቷ መጥተው ለሚኖሩ ዜጎች 80 ሺህ ዩሮ እንደምትከፍል ገለጸች፡፡ ሀገሪቱ ደሴቲቱ ሰው አልባ እየኾነች መምጣቷን ተከትሎ ነዋሪዎችን ለማበረታታት ሽልማት አዘጋጅታለች። ወደ ደሴቶቹ መሄድ የሚፈልጉ ሰዎች ከሐምሌ አንድ ጀምሮ ማመልከት ይችላሉ ተብሏል። የአውሮፓ ሀገራት የሕዝብ ብዛት በየጊዜው እያሽቆለቆለ መምጣቱን ተከትሎ በየጊዜው ዜጎቻቸው ልጆን እንዲወልዱ የተለያዩ ማበረታቻዎችን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡ አሁን ደግሞ አየርላንድ ሰው አልባ ወደ የኾኑ ደሴቶቿን በሰዎች ለመሙላት አዲስ ፖሊሲ ማዘጋጀቷን አስታውቃለች፡፡ አየርላንድ ባዘጋጀችው አዲሱ ደሴቶችን በነዋሪዎች የመሙላት እቅድ መሠረት ዳጎስ ያለ የገንዘብ ሽልማት ያዘጋጀች ሲሆን ወደነዚህ ደሴቶች ለሚያመራ ሰው 80 ሺህ ዩሮ እንደምትሰጥ ተገልጿል፡፡ 30 ሰው አልባ የኾኑ ደሴቶች ያሏት አየርላንድ በየጊዜው የነበሯቸውን ነዋሪዎች እያጡ አሁን ላይ ወደ ምድረ በዳነት እየተቀየሩ ነው የተባለ ሲኾን በቀጣይ ወደ ደሴቶቹ የሚሄዱ ሰዎችን ለመጨመር አዲስ እቅድ ማውጧን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡ እንደ ዘገባው ከኾነ እነዚህ ሰው አልባ የአየርላንድ ደሴቶች ከሌሎች ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች እና መንገዶች የሏቸውም፡፡ ሀገሪቱ ወደደሴቶቹ ለሚያቀኑ አዳዲስ ነዋሪዎች ገንዘቡን በመስጠት ሕይወት እንዲጀምሩ፣ ንብረቶችን እንዲያፈሩ እና ሌሎች ለሕይወት አስፈላጊ የኾኑ ቁሳቁሶችን እንዲያሟሉባቸው የማድረግ እቅድ አላት ተብሏል፡፡ በዚህም መሰረት ከፈረንጆቹ ሐምሌ አንድ ጀምሮ ወደ አየርላንድ ደሴቶች በመሄድ መኖር የሚፈልጉ ዜጎች ማመልከት እንደሚችሉ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡ የስፔን፣ ጣልያን እና ፊንላንድ መንግሥታት ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱ፣ ወደ ገጠር ከተሞች ሄደው እንዲኖሩ የተለያዩ የገንዘብ ስጦታዎችን ካዘጋጁ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን!! በክርስቲያኖች ዘንድ ጥምቀት...

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የአርቲስት ነጻነት ወርቅነህ ስርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባኦት ቅድስት...

በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም ዓይናቸው በጽኑ መታመሙን ጠበቃቸው ገለጹ

ከሁለት ዓመት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት መምህርት መስከረም አበራ...

ንግድ ባንክ “ስታርፔይ” የተሰኘ አዲስ መተግበሪያ ይፋ አደረገ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንክ ሥርዓቱን ይበልጥ ዘመናዊና ቀልጣፋ...