4ኛ የስራ ዘመን፣ 1ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደዉ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አቶ አብዱላሂ አደንን የአስተዳደሩ ከንቲባ አድርጎ ሰይሟል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት፣ 1ኛ ዓመት 4ኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ፣ የልዩ ልዩ አስተዳደር ካቢኔዎችን ሹመት አፀደቀ።
- በዚሁ መሠረት፦
ሌሊሴ አህመድ – የሴቶች፣ ሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
አቶ ግርማ ተሰማ – የፓብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሀየር ሀጂኑር – የኮንስትራክሽን እና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ
አብዱሰላም አህመድ – የፍትሕ፣ ሕግ እና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
አቶ አብዱሰመድ መሐመድ – የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
ስንታየሁ ማሞ – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሡልጣን አሊይ – የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
ዶ/ር ፈቃዱ በየነ – የሥራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
ዶ/ር ዩሱፍ መሐመድ – የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ
ዶ/ር አብዱሰላም መሐመድ – የመሬት ልማት እና ማኔጅመንት ቢሮ ኃላፊ
አቶ መህዲ መሐመድ – የግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድን እና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሾመዋል።
በተጨማሪ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሃር የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።
ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን ኡስማንን የምክርቤቱ አፈ-ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።
አቶ ሀርቢ ቡህ ዋርሰሜ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ
ክብርት ወ/ሮ አንድነት ሀይሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ፀሀፊ
