የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አገኘ

Date:

ኢትዮጵያ ቡና ከ37 ሚ ብር በላይ፣ ባህርዳር ከተማ ከ35 ሚ. ብር በላይ አግኝተዋል

የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን የሆነው የኢትዮጵያ መድን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ አግኝቷል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማህበር፣ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከብሮድካስትና ስም ስያሜ መብት የሚያገኙትን ክፍፍል ይፋ አድርጓል።

በዚህም ዓመቱን በአሸናፊነት ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ መድን፣ 40 ሚሊየን 295 ሺህ ብር በላይ ማግኘቱ ተገልጿል።

በሊጉ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና፣ 37 ሚሊየን 703 ሺህ ብር ያገኘ ሌላኛው ክለብ እንደሆነ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ባሕር ዳር ከተማ 35 ሚሊየን 281 ሺህ 37 ብር ማግኘቱን የገለጸው አክሲዮን ማህበሩ፤ በአጠቃላይ በ2017 የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ ለሆኑ ክለቦች 428 ሚሊየን 846 ሺህ ብር ማከፋፈሉን አስታውቋል፡፡

(WMCC)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...