
ያዬ – ስልኩ ይጠራል – ግን አይነሳም። ቤተሰቦቹ ኦሎምፒያ አደባባይ የሚገኘው ፐርፕል ሕንጻ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር (ላፓሪዚያን ቁጥር 1 ግቢ) – ቤቱ ደረሱ።
አንኳኩ …
ዛሬ ጠዋት በሩን የሚከፍት ሰው አልተገኘም። ስልኩን በተደጋጋሚ ሞከሩት፤ አሁንም ይጠራል።
ፖሊስ ተጠራ …
በሩ ተሰብሮ ተገባ።
የጥበብ ዋርካው ወለል ላይ ወድቋል።
“ቆሜ ልመርቅሽ” የተሠኘው ዘፈን ግጥም ደራሲ እንዲሁም የበርካታ ግጥምና ዜማዎች ፕሮዉዲሰር #ያየህይራድ አላምረው ( ያዩ ) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ትልቅ አስተውፅኦ ያበረከተ የጥበብ ሰው ነበረ።
ያዬ – (የዝነኛው ኳስ ተጫዋች #አንተነህ_አላምረው ታላቅ ወንድም ነው)
ከብዙ ጥቂት ሥራዎቹን ለማስታወስ ….
“ወዳንተ ስልከው — አማላጁን ሁሉ ፣
ከደጃፍህ ደርሶ —- ይመለሳል አሉ ።
ካንተ የሚያስታርቀኝ —- ሁነኛ ወዳጅህ ፣
እንዴት ያለው ሰው ነው —- የሚቆም ከደጅህ ።
የሚለው ተወዳጅ ዘፈን ያለበትን #የአስቴር አወቀን
“#የሰርጌ ትዝታ ፣ ወይም #ትውስ አለኝና” በሚል የሚታወቀውን ካሴት ሙሉ ግጥም ሠርቷል።
የፀሐዬ ዮሀንስ “እወራረዳለሁ ፣ ምን ይወጠኝ ነበር”፣
የሀይልዬ “የኢትዮጵያ አምላክ ፣
የኩኩ ሰብስቤ “ኢትዮጵያ ( ይታየኛል ) ፣
የፀጋዬ እሸቱ “10ቱ ትዕዛዛት” ፣
የታደለ ሮባ “ባቲና ብሉዝ” እንዲሁም
የክቡር ዶክተር አርቲስት #ጥላሁን ገሠሠ “ቆሜ ልመርቅሽ” የሚለውን ማውሳት እችላለሁ።
ለኤሊያስ ተባባል ፣
ለጌራወርቅ ነቃጥበብ እና ለሌሎችም በርካታ ግጥሞችን የሰጠ ሲሆን በተለይ ደግም ልክ እንደ የፍቅር አልበም በየቤታችን ገብቶ ያጣጣምነውን በኤችአይቪ ዙሪያ በርካታ ተወዳጅ አርቲስቶች የተሳተፉበትን “#እንኖራለን ገና ” የሚለውን አልበም በማስተባበርና ድርሰቶች በመስራት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረከተ ታላቅ ባለሙያ ነበር።
ከቀድሞው ጀግናው የኢትዮጵያ ሠራዊት ቤተሰብ የተገኘ አንጋፋ እና በሳል የዘፈን ግጥም ደራሲያን አንዱ ነው።
የዘፈን ግጥም ፀሐፊ፣ ፕሮዲዮሰር ያየህ ይራድ አላምረው ነበር።
ስለሀገሩ ኢትዮጵያ በሠራቸው ጥቂት ሥራዎች ላይ ላተኩር በኩኩ ሰብስቤ ሥራ ውስጥ የሀገሩን ኢትዮጵያ ዳግም ታላቅነት እና ትንሳኤዋን አስመልክቶ እንዲህ ይላል …
የሺ አመታት የአፍሪካ ገናና
ተከብራ የኖረች በዓለም ዙሪያ ገና
ኢትዮጵያ ዳግም እንደገና
ይታየኛል የአገር አውራ ሆና ይላል
~በኃይልዬ ታደሰ
ሥራ ውስጥ
የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል ሳይውል ሳያድር
ይጥልላታል ጠላቷን እባንዲራው ስር
አይቀር አንድ ቀን መድረሱ ወቅቱን ጠብቆ
ማሪኝ ይላታል ጠላቷ
እጇ ላይ ወድቆ
~በታደለ ሮባ እና ፋንታ በሌ
(ባቲ እና ብሉዝ)የቅብብል ሥራ
አባም እንዳልልህ ዘመናዊ
ፀጉር አወራረድህ ባህታዊ
ከየት ነው የመጣህ ምናዊ
~በኢትዮጵያው የሙዚቃ ንጉሥ ጥላሁን ገሠሠ የመጨረሻ ሥራ ውስጥ
ቆሜ ልመርቅሽ ተቀበይኝ እማ
ህይወትን መርቀሽ
ሠጠሽኝ እኔማ
ይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ በዓለም ኢትዮጵያ እድሜ ላንቺ ያላየሁት የለም
አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየው እና
ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና
ከእርሱ በላይ ስራዎቹ የሚታወቁት #ያየህይራድ አላምረው/
በርካታ የዘፈን ግጥም እና ዜማዎችን ሰርቷል !
ወዳጆቹ #ያዩ እያሉ ነው የሚጠሩት ! ሙያተኛን ለማገዝ ቅን ሰው እንደሆነ እመሰክራለሁ። ዝና እና እውቅና የሚያጓጓው ሰው ስላልሆነ ሚዲያ ላይ ብዙም አይታይም!!
ብዙ ሰዎች በስም እንጂ በአካል እንደማያውቁት ይናገራሉ ! ለሀገሩ ለ #ኢትይጵያ ስላለው ፍቅር በየሚዲያው ባይናገርም ለተለያዩ ድምፃውያን የሰጣቸው ግጥሞች ምስክሮቹ ናቸው !
ለድምፃዊ #ፀጋዬ እሸቱ ፲ቱ ትዕዛዛት ላይ የፃፈው ግጥም ሁሌም ያስገርመኛል !
” የፈጣሪ ትዕዛዝ ቃሉ ቢከበር
ወንጀለኛ መቅጫ ህግም ባልነበር
ከምድራዊው ፖሊስ ከሕግ አስከባሪ ፣ እንፍራ ፈጣሪን
ስለ እራሱ ምንም ነገር መናገር አይፈልግም። ሰው ሥራዌቼን እንጂ እኔን ማወቅ አያስፈልገውም ይላል።
የኢትዮጵያ አምላክ ይፈርዳል!
ድምፃዊ፦ ኃይልዬ ታደሰ
ግጥምና ዜማ፦ ያየህይራድ አላምረው
ዜማ ፦ ሞገስ ተካ ግጥም ፦ ያየህይራድ አላምረው
“……የሕይወቴ ብርሃን የጨለማው መብራት ፣
አንቺው መሆንሽን ልግለፀው በመኩራት ።
“ላንተ ትሁን” ብሎ የፈጠረልኝን ፣
ላክብር ፣ ላመስግነው አንቺን ያደለኝን ።……”
— ፀሐይ ዮሐንስ
የደስደስ
ተሾመ ወልዴ
ቅንብር ሙላቱ አስታጥቄ
አጃቢ ኢትዮ እስታር ባንድ
ግጥም ያየህይራድ አላምረው
ቆሜ ልመርቅሽ
ጥላሁን ገሠሠ
ቆሜ ልመርቅሽ (ሙሉ ግጥም
ተቀበይኝ እማ ቆሜ ልመርቅሽ
ሕይወትን መርቀሽ ሰጥተሽኝ እኔማ
ይህ ቀረኝ የምለው የሚቆጨኝ በዓለም፣
ኢትዮጵያ ዕድሜ ላንቺ ያላየሁት የለም።
አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና፣
ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና።
ትንቢትሽ ይፈፀም ከመሬት ጠብ አይበል፣
ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ ገድልሽ ይንበልበል፤
ሰንደቅሽ ከፍ ይበል ይቁም ለዘላለም፣
ሰላም፣ ጥጋብ፣ ደስታ፣ ይታይብሽ ዓለም።
ሴራው ይክሸፍበት የመታብሽ አድማ፣
እጁን ሣር ያድርገው ጉልበቱን ቄጤማ፤
ካቀባበለብሽ ብረት ከደገነ
አምላክ ያግዝልሽ ላንቺ የወገነ፤
ፀሎትሽ ይሰማ አምላክ ይለመንሽ፣
ፈተናው አይለቅ የሚፈታተንሽ፤
አንገትሽ ራስሽን ችሎ ልየውና
ማግስቱን ይውሰደኝ አስር ሞት ይምጣና፤
በሰው ሀገር ምድር ለተበተኑት፣
ለልጆችሽ ሁኚ ዞሮ መግቢያ ቤት፤
በዓለም አደባባይ ከመንግሥታት ደጅ
ሞልቶሽ ተርፎሽ እንጂ ጎድሎብሽ አትሂጅ፤
ጎተራሽ አይጉደል አይድረቅ ሌማትሽ
ከክፉ ሰውሮ ያድንሽ እምነትሽ፤
ላንቺ የማይተኙ የማያንቀላፉ፣
ብን ይበሉ እንደጉም ከምድረ ገጽ ይጥፉ፤
ካረግንልሽ በላይ የምትሆኝልን፣
መጠሪያ እናታችን አንቺው ቆዪልን !!!
ግጥም :ያይራድ አላምረው
ዜማ : ሞገስ ተካ
ቅንብር : አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ ምንጭ: – Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)