በበርካታ የባህል ሙዚቃ ዜማዎቿ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘችው ድምፃዊት ራሔል ዮሐንስ ሕይወቷ ማለፉን ቤተሰቦቿ ገልጸዋል።
ድምፃዊቷ ያጋጠማትን የጤና እክል ተከትሎ በሕክምና ስትረዳ ቆይታለች።
ራሔል ዮሐንስ በግሏ እናከተለያዩ ድምፃውያን ጋር በመሆን በርካታ ተወዳጅነት ያገኙ ሙዚቃዎችን ሠርታለች።
በሙዚቃዎቿ ከድምፃዊነቷ ባለፈ፣ በአንዳንዶቹ ላይ በግጥም እና በዜማ ድርሰትም አስተዋፅኦ ታደርግ ነበር።
ራሔል ዮሐንስ ከሠራቻቸው ሙዚቃዎቿ መካከል “ምኒልክ”፣”ኢትዮጵያ”፣ “አራዳ”፣ “እንደ ኢየሩሳሌም”፣ “ትዝታ”፣ “አንቺ ባለድሪ”እና “አየር ኃይላችን” የመሳሰሉት ተወዳጅነት አግኝተውላታል።
