ገዳ ባንክ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ አተረፍኩ አለ

Date:

ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ113 በመቶ እድገት አሳይቷል  ብሏል።

ገዳ ባንክ ይህንን ያለው የ2018 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም እና የተገኙ ውጤቶችን በማስመልከት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

በ2018 በጀት ዓመት ባንኩ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ከታክስ በፊት ማትረፉን የተናገረ ሲሆን 12.6 ቢሊየን ብር ደግሞ ተቀማጭ ሀብት እንዳለው አንስቷል።

ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 64 በመቶ እድገት አሳይቷል ሲሉ የባንኩ ፕሬዚደንት አቶ ወልዴ ቡልቶ ተናግረዋል።

ጠቅላላ ሀብቱ 16.5 ቢሊየን ብር ደርሷል፣  ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር ደግሞ በ64 በመቶ እድገት አሳይቷል ተብሏል።

በሌላ በኩል በአጠቃላይ 110 ቅርንጫፎች እንዳሉት የተናገረው ገዳ ባንክ ስራ 10ሩ ቅርንጫፎች በበጀት ዓመቱ ወደ ስራ የገቡ መሆናቸውን ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ባንኩ ዋና መስሪያቤት ለመገንባት የሚያስችለውን የመጀመሪያ ሂደቱን መጨረሱን የሰማን ሲሆን የወደፊት ህንፃ ፍላጎት፣ የአዋጭነት ጥናት፣ የህንፃው ዲዛይንን አጠናቅቆ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ በመሸጋገር የጨረታ ሂደት ላይ ደርሷል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኢትዮጵያ 50 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች የንፁህ መጠጥ ውሃ እንደማያገኙ ተነገረ

በኢትዮጵያ የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በበቂ ሁኔታ ለማሳካት የሚያስችል...

እስራኤል የኢራን ተደራዳሪዎችን ለመግደል እያሴረች እንደነበር ተዘገበ

አሜሪካና ኢራን ወሳኝ የሆነውን የተኩስ አቁም ስምምነት በደረሱበት እስራኤል...

ከኡጋንዳ ወደ ኢትዮጵያ የመጀመሪያው በፋብሪካ የተቀነባበረ  የበሬ ሥጋ ንግድ ተጀመረ

‘ራንቸርስ ፋይነስት’ የተባለው የኡጋንዳ የግል ሥጋ አቀናባሪ ኩባንያ፣ በየወሩ...

ክፍያ በመቀበል የባንክ ሂሳብ ቁጥራቸውን የሚያከራዩ በዝተዋል

የባንክ ሂሳብ ቁጥርን በመሸጥና በማከራየት የሚፈጸም የማጭበርበር ወንጀል መበራከቱን...