ጊዜያዊ አስተዳደር ለውጥ አያመጣም ሲል ሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ገለፀ

Date:

ፓርቲው በይፋዊ ገፁ ላይ ባወጣው መግለጫና ትናንት በመቀሌ ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ በጄኔራል ታደሰ ወረዳ የሚመራው ጊዜያዊ አስተዳደር የህወሀት አንጃ ስልጣኑን እንዲቆጣጠር ፈቃድ እንደሰጠው ገልጿል፡፡

በፕሪቶሪያ ስምምነት አንቀፅ 10 መሰረት የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር ሁሉን ያካተተ እንዲሆን የተደነገገ ቢሆንም አሁን የተመሰረተው ካቢኔ ግን ይህንን አለማሟላቱን አስታውቋል፡፡

‹‹አሁን ያለው የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ በዶክተር ደብረፅዮን ለሚመራው ህወሀት ተላልፎ የተሰጠ ነው›› ያለው ፓርቲው እንደምሳሌም የከተማ ልማት ቢሮ፣ የውሀ ሀብት ቢሮ፣ የትምህርት ቢሮና የጤና ቢሮ እንዲሁም ሌሎች ስልጣኖች በዚህ ቡድን መያዛቸውን አስረድቷል፡፡

ጨምሮም ‹‹በአንድ ሀይል የበላይነት የተያዘው ጊዜያዊ አስተዳደር ለትግራይ ዘላቂ ለውጥ ማምጣት አይችልም›› ያለው ሳልሳይ ወያነ እንዲህ አይነቱ ድርጊት ወደ አምባገነንነት ሊያመራ እንደሚችልም አሳስቧል፡፡

በመሆኑም ጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔውን ሁሉን ባካተተ መልኩ እንዲቀይር ጥሪ አቅርቧል፡፡

ከጋዜጠኞች ‹‹እንዲህ አይነት ቅሬታ ከማቅረባችሁ በፊት ከጄኔራል ታደሰ ጋር በጉዳዩ ላይ ተወያይታችሁ ነበር ወይ›› የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው የፓርቲው አመራሮች ‹‹ጉዳዩን በተመለከተ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ለመነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡›› በማለት መልሰዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ ለኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ደብዳቤ ላከች

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ለኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር...

ዓመታዊ ግብርን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማሳወቅና መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ተዘረጋች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከእንግዲህ የደረጃ «ሀ» ግብር...

62ኛው የባህል ማዕከል ምሽት አንጋፋዋን ጋዜጠኛ የመዓዛ ብሩን ዘክሯል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፥ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ...

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ሀኪም ቁጥር አራት ብቻ ናቸው

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በሰፊው እንደሌለ እና...