የደርግ መንግስት የወደቀበት ግንቦት 20 በትግራይ ክልል ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። ባለፈው ዓመት የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አውጥቶት በነበረው የሃይማኖታዊ እና ህዝባዊ በዓላት አዋጅ መሰረት፥ ግንቦት 20 ከህዝባዊ በዓላት ዝርዝር መሰረዙ ይታወሳል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ዕለቱ በመቐለ፥ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣናት እና የህወሓት መሪዎች በተገኙበት እየተከበረ ይገኛል። በዚሁ አከባበር ንግግር ያደረጉት የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ የደርግን መንግስት ለመጣል በተደረገ ትግል “ትግሉን ለድል ያበቃችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ለ34ተኛ ዓመት የደርግ ውድቀት እና የኢትዮጵያ ህዝቦች ድል አደረሳችሁ” ብለዋል።
(dw) መቀሌ
