ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

Date:

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።

ኢንስትትዩቱ ከምድር እስከ ህዋ ድረስ የሚገኙ መረጃዎችን በመተንተን የምርምር ስራዎችን የሚያከናውን ተቋም ነው።

የምርምር ስራዎቹ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ እየተተነተኑ ቅድመትንበያና የትንበያ ስራዎችን በመስራት ለሚመለከታቸው ተቋማት እንዲጠቀሙበት ያስችላል።

የጂኦ ስፓሻል ጥናትና ምርምር በተለያዩ ዘርፎች የተዋቀረ ሲሆን ዛሬ በየሥራ ክፍሎቹ የሚከናወኑ የመረጃ ትንተና እና ምርምር ስራዎች ምልከታ መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።

ኢቢሲ                                                             

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...