ፌዴራል ፖሊስ ከተባበሩት መንግሥታት የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን በድጋፍ አገኘ

Date:

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ ከተባበሩት መንግሥታት የሴፍቲና የሴኩሪቲ ዲፓርትመንት ለወንጀል መከላከል ሥራ አጋዥ የሆኑ ዘመናዊ ኮምፒውተሮችንና የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን በድጋፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በተከናወነው የርክክብ ሥነ-ሥርዓት፣ የዲፓርትመንቱ ኃላፊ ሚስተር ፕሪንስ ብሩስ መሣሪያዎቹን ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ አስረክበዋል።

ምክትል ኮሚሽነሩ በዚሁ ወቅት በድጋፍ የተገኙት ቁሳቁሶች ተቋሙ እያከናወነ ላለው የወንጀል መከላከል ተግባር ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖራቸው ገልፀዋል።

የዲፓርትመንቱ ኃላፊ ሚስተር ፕሪንስ ብሩስ በበኩላቸው፤ ተቋማቸው ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ድጋፍ በማድረጉ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፣ በቀጣይም በወንጀል መከላከል ዙሪያ በትብብር ለመሥራትና ሌሎች መሰል ድጋፎች እንደሚደረጉ መናገራቸውን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...