“ፓኪስታን ትክክለኛ አስታራቂ አይደለችም” ኢራን!

Date:



የኢራን ህግ አውጪ ኢብራሂም ሬዛኢ ከአሜሪካ ጋር እየተካሄደ ባለው ውይይት ፓኪስታን ትክክለኛ አስታራቂ አይደለችም ሲሉ ተናግረዋል።

ኢብራሂም ሬዛኢ ይህንን ያሉት የሀገራቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ የሠላም ድርድሩ እንዲሳካ ከኦማን እስከ ኢስላማባድ ድረስ ደፋ ቀና እያሉ በሚገኙበት ሰዓት ነው።

ዳሽቴስታንን ወክለው የኢራን ብሔራዊ ደህንነትና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ሆነው የሚያገለግሉት ኢብራሂም ሬዛኢ ፓኪስታን ለሽምግልና የሚያስፈልገው ተዓማኒነት እንደሌላት ገልፀዋል።

በኤክስ ገፃቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ፓኪስታን ጥሩ ጎረቤት መሆኗን ጠቅሰው ነገር ግን ለድርድር ምቹ አይደለችም ምክንያቱም ለአሜሪካ ታዳላላች ሲሉ ፅፈዋል።

አስታራቂ ገለልተኛ እንጂ ወደ አንዱ ወገን ያደላ መሆን የለበትም የሚሉት ሬዛኢ ፓኪስታን ዋሽንግተንን በግልፅ ከመተቸት መቆጠቧን አያይዘው አንስተዋል።

ኢብራሂም ሬዛኢ ፓኪስታን አሜሪካ በሌባኖስና በታገዱ ንበረቶች ላይ ያላሟላቻቸውን ቃሎች እንድትፈፅም ግፊት አላደረገችም ሲያልፍም ችግሩን አጉልታ አላሳየችም ብለዋል።

የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከሰሞኑ በኢስላማባድ በነበራቸው ቆይታ ከፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼህባዝ ሻሪፍ ጋር የተወያዩ ሲሆን በኦማን ቆይታቸውም ከሱልጣን ሀይተም ቢን ታሪቅ አል-ሰይድ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

የኢራን ሚዲያ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ውይይቶች ከኑክሌር ጉዳይ ባሻገር የሚያልፉ ሲሆን ይህም ለሆርሙዝ የባህር ሰርጥ አዲስ የህግ ማዕቀፍ ሀሳቦችን፣ የካሳ ጥያቄዎችን፣ ተጨማሪ ወታደራዊ እርምጃን ለመከላከል ዋስትናዎችንና የአሜሪካ የባህር ላይ ገደቦችን ማንሳትን ያካትታል ተብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ...

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...