ሁቲዎች የሳዑዲ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ገለጹ

Date:

የኢራን አጋር የሆኑት ሁቲዎች የሳዑዲ አራምኮ ጃዛን ነዳጅ ማጣሪያን እሁድ ዕለት ማጥቃታቸውን ተናገሩ።

ሁቲዎች ጥቃቱን የፈጸሙት ሳዑዲ ከቱርክ እና ከፓኪስታን ጋር ወታደራዊ ትብብር ከፈረመች ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።

የሳዑዲ ኢነርጂ ሚኒስቴር በነዳጅ ማጣሪያው አካባቢ እሳት መቀስቀሱን ይፋ ካደረገ በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ገልጿል።

ነገር ግን እሳቱ በምን ምክንያት እንደተከሰተ ያለው ነገር የለም።

የነዳጅ ማጣሪያው በደቡብ ምዕራብ ሳዑዲ አረቢያ የሚገኝ ሲሆን በቀን 400 ሺህ በርሜል ድፍድፍ ዘይት ያጣራል።

በእሳት ቃጠሎው ስለደረሰው ውድመት የተባለ ነገር የለም።

ሁቲዎች ማጣሪያውን ያጠቁት ድሮን ተጠቅመው መሆኑን ቃል አቀባያቸው ያህያ ሳሬ በኤክስ ገጻቸው ላይ አጋርተዋል።

ኢራን እና አጋሯ የሆኑት የሁቲ ታጣቂዎች የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ በሳዑዲ አረቢያ እና በሌሎች የባሕረ ሰላጤው አገራት ላይ ጥቃት የሚፈጽሙ ሲሆን የመርከቦች እንቅስቃሴ ላይም እገዳ ጥለዋል።

የአራምኮ ኃላፊ የሆኑት አሚን ናስር ባለፈው ሳምንት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኩባንያው ተቋማት ላይ የሚደርሰው ጥቃት የምርት መስተጓጎል መፍጠሩን ተናግረው በፍጥነት ወደ ማምረት ተግባራችን እንመለሳለን ብለዋል።

አራምኮ የዓለማችን ቀዳሚ ነዳጅ ላኪ ኩባንያ ነው።

ኃላፊው አክለውም ጥቃቱ በቁስ ላይ ወይም በፋይናንስ ረገድ ያደረሰው ጉዳት የለም ብለዋል።

የኢራን ጥቃት የዓለም የነዳጅ አቅርቦትን ካስተጓጎለ በኋላ አርብ ዕለት ሳዑዲ አረቢያ ከቱርክ እና ፓኪስታን ጋር ወታደራዊ ትብብር ተፈራርማለች።

አገራቱ በዚህ ስምምነት መሠረት “ከሦስቱ አገራት በአንዱ ላይ የሚፈጸም ማንኛውም የትጥቅ ጥቃት በሁሉም ላይ እንደተፈጸመ ጥቃት ይቆጠራል” ብለዋል።

አክለውም ይህ የጋራ ስምምነት “ማንኛውንም የጥቃት እርምጃ ለመከላከል የሚያስችል የጋራ የመከላከል አቅምን የማጠናከር” ዓላማ አለው ብለዋል።

BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢትዮጵያዊዉ የመጀመሪያው የአይን ሐኪም ዶክተር ጳውሎስ አረፉ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን...

ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች በዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር 3ኛ ወጡ

በካናዳ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ የተሳተፉት የኢትዮ...

በዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 2ኛ የወርቅ ሜዳሊያ አገኝች

በሴቶች 3 ሺህ ሜትር የተወዳደሩት  ዮርዳኖስ ጽጋብ እና ሽቶ...

“አዳም አንድ ደራሲ የሚያስፈልጉት ሁሉም ግብዓቶች ተሟልተው ያሉት ፀሐፊ ነው”

አዳም ረታ ሥራዎቹን ለአንባቢ ማድረስ የጀመረው ከ1970ዎቹ አንስቶ ነው።...