ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች የሚያጋልጥ 90 ኩንታል በርበሬ ተወገደ

Date:

በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 በሚገኝ የገበያ ማዕከል ውስጥ፣ ለከፍተኛ የጤና ጉዳት ሊዳርግ የሚችል 90 ኩንታል የ“በሬዳ ባልትና” በርበሬ ገበያ ላይ ሳይሰራጭ መወገዱን የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን አስታወቀ።

ምርቱ በከፍተኛ ሁኔታ በአፍላቶክሲን (ሻጋታ) የተጠቃ ሲሆን፣ ይህም የሆነው አምራቹ 70 ኩንታል በርበሬ ላይ 20 ኩንታል ለውዝ በመቀላቀል እርጥበት ባለው መደብር ውስጥ በማከማቸቱ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የተበከለ ምርት ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች የሚያጋልጥ በመሆኑ፣ ባለሥልጣኑ ምርቱ ወደ ህዝብ ሳይደርስ የማስወገድ እርምጃ ወስዷል። በድርጅቱ ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ በሰው ጤና ላይ አደጋ የደቀነው ግለሰብም ለሕግ አካላት ተላልፎ ተሰጥቷል። ድርጊቱ የተፈጸመው አላግባብ ትርፍ ለማግኘት በሚፈልጉ ስግብግብ ነጋዴዎች የሞራል ጉድለት መሆኑን የባለሥልጣኑ ኃላፊዎች ጠቁመዋል።

የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን መሰል የምግብ ክለሳና የባዕድ ነገር መቀላቀል ተግባራትን ለመከላከል ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል። ሕዝቡም ማንኛውንም የባልትና ምርቶች ሲገዛ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ጤናውን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...