ሊቨርፑል የባየር ሊቨርኩሰኑን የቀኝ መስመር ተከላካይ ጄረሚ ፍሪምፖንግን በ30 ሚሊዮን ዮሮ የዝውውር ሂሳብ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ።
በስምምነቱ መሠረት ፍሪምፖንግ በሊቨርፑል ቤት ለ5 ዓመታት የሚቆይ ይሆናል።
ሊቨርፑል የአንፊልዱ ኮከብ ትሬንት አሌክሳንደር ወደ ማድሪድ መቀላቀሉን ይፋ ካደረገ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ኔዘርላንዳዊውን ኢንተርናሽናል ተጫዋች ማስፈረሙን አረጋግጧል።
ሁለገቡ የቀኝ እግር ተጫዋች ፍሪምፖንግ በአርኔ ስሎት ቡድን ውስጥ የአሌክሳንደር አርኖልድ ምትክ ሆነው ይጫወታሉ ተብለው ከሚጠበቁ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሆኗል።
በልጅነቱ በማንቸስተር ሲቲ ቤት ሰልጥኖ ያደገው ሆላንዳዊው በ2021 ወደ ሊቨርኩሰን ከመዛወሩ በፊት በ2019 ለሴልቲክ ተጫውቷል።
ፍሪምፖንግ በሊቨርፑል ቤት የሀገሩ ኮከቦች ከሆኑት ቨርጂል ቫን ዲጅክ፣ ኮዲ ጋክፖ እና ራያን ግራቨንበርች ጋር ተቀላቅሏል።
